በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ተግዳሮቶች
ሰኞ፣ መጋቢት 19 2008ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ በውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት የሚሳተፉ ሃገራት ውስንነት አስጊ መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎች አሳሰቡ ። በኢትዮጵያ ቀጥተኛ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ተግዳሮቶች ላይ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ ውይይት ፣ በሃገሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ ሃገራት ውስን በመሆናቸው በዘርፉ እንቅስቃሴ ላይ ተፅእኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ባለሞያዎቹ ስጋታቸውን ገልፀዋል ። ምንም እንኳን የመዋዕለ ንዋይ ፍሰቱ ከቀድሞው አሁን እያደገ ቢሄድም ሊያዘናጋ የሚገባ አለመሆኑንም ባለሞያዎች አሳስበዋል ። ውይይቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ