1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስአፍሪቃ

በኢትዮጵያ ደቡባዊ ግዛት ከሰማይ ተቀጣጥሎ የታየው ባዕድ ነገር ምንነት

ዓርብ፣ ጥር 2 2017

እነዚህ ባዕድ ነገሮች ወደ መሬት ስወድቁ “አስትሮይድ” በመባልም ይጠራሉ፡፡ ክብደታቸው ቀለል ያለ ሆነው በአየር ላይ ተቃጥለው በነው ሲያልቁ ደግሞ “ሚቲዮራይት”ይባላሉ፡የሆነ ሆኖም በትናንትናው እለት በኢትዮጵያ ምድር ሰማይ ላይ የታየው ተቀጣጣይ ነገር በሰው ሰራሽ አሊያም በዚህ በተፈጥሮ ክስተት የሚፈጠር ሊሆን እንደምችል ነው በባለሙዎቹ የተገመተው

ደቡብ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሰማይ ተቀጣጥሎ የታየው ባዕድ ነገር ምንነት
ደቡብ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሰማይ ተቀጣጥሎ የታየው ባዕድ ነገር ምንነትምስል Allan G. Madelar/AP/picture alliance

ደቡብ እና ደቡብ ምዕራባዊ የኢትዮጵያ ክፍል ህዋ ላይ የታዩ ተቀጣጣይ ቁሶች ምን ይሆኑ ?

This browser does not support the audio element.

ትናንት ማምሻውን በኢትዮጵያ ደቡባዊ አጋማሽ አከባቢዎች ከሰማይ ተቀጣጥሎ ወደ ምድር ሊወድቅ ሲል ታይቷል የተባለውን ባዕድ ነገር በማስመልከት አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የስነከባቢ አየር ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ገመቹ ፋንታ፤ ኢንስቲትዩታቸው ምስሉን በመውሰድ ሳይንሳዊ ትንታኔ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ባለሙያው እንዳሉት እየተቃጠለ ወደ ምድር ስጓዝ የታየው ባዕድ ነገር በሁለት መልኩ የሚገለጽ ነው ይላሉ፡፡ “አንደኛው በሰው ሰራሽ የስፔስ (ከባቢያዊ አየር) ቁሶች ምክንያት የተከሰተ ሊሆን ይችላል” ያሉን ባለሙያው ይህም “በሰዎች የሚመጥቁ ሳተላይቶች የአገልግሎት ጊዜያቸውን ስጨርሱ ተሰባብረው ወደ ከባቢ አየር ልወድቁ ይችላሉ” ሲሉ ቀዳሚውን መላምት አስቀምጠዋል፡፡ ምናልባትም ሳተላይቶችን ለማምጠቅ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሮኬቶች ስብርባሪም ሊሆን እንደምችል ጠቁመዋል፡፡

በአፍሪቃ የህዋ ሳይንስ ተቋም ሰለመገንባት የመከረው አውደ ጥናት

እየተቀጣጠሉ ወደ ምድር የሚወድቁት ባዕድ ነገሮቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ በሚል የተቀመጠው ሁለተኛው መላምት ደግሞ በተፈጥሮአዊ የህዋ አካላት ላይ የተከሰተ ሊሆን ይችላል የሚል ነው፡፡ ይህም ተፈጥሮአዊ ክስተት መሆኑ ነው፡፡ “በተፈጥሮአዊ የህዋ አካላት ምክንያት የሚከሰተው በፕላኔት አፈጣጠር እና ከሶላስ ሲስተም አፈጣጠር ጋር ተያያዘ ነው ሊሆን ሚችለው” የሚሉት ዶ/ር ገመቹ “ይህም በፕረላኔት ውስጥ የሚሽከረከሩ አለቶች ስብርባሪ ሊሆን ይችላል” በማለት ገለጻቸውን ቀጥለዋል፡፡ እነዚህ በሰበቃ የሚሰባበሩ አለቶች መሬት ላይ ስደርሱ መጠናቸው እጅጉን እንደሚቀንስም አብራርተዋል፡፡

የተባባሰው የህዋሓት ውዝግብ

እነዚህ ባዕድ ነገሮች ወደ መሬት ስወድቁ “አስትሮይድ” በመባልም ይጠራሉ፡፡ ክብደታቸው ቀለል ያለ ሆነው በአየር ላይ ተቃጥለው በነው ሲያልቁ ደግሞ “ሚቲዮራይት”ይባላሉ፡፡ የሆነ ሆኖም በትናንትናው እለት በኢትዮጵያ ምድር ሰማይ ላይ የታየው ተቀጣጣይ ነገር በሰው ሰራሽ አሊያም በዚህ በተፈጥሮ ክስተት የሚፈጠር ሊሆን እንደምችል ነው በባለሙዎቹ የተገመተው፡፡ ከዚህ በፊት ባለፈው ክረም ጅማ አከባቢ ተመሳሳይ ባዕድ ነገር እንደመብረቅ ሆኖ መውደቁን በማስታወስ ከትናንቱ ክስተት ጋር ምን ያመሳስላቸዋል የተባሉት የስነከባቢ ተመራማሪው፤ “ጅማ የወረደው ወደ ምድር ወድቆ ታይቷልና ያም ቢሆን ትክክለኛ አስተሮይድ ነው ወይ የምድር አለት ነው ብሎ ለመለየት በኢትዮጵያ አዳጋች ነው” በማለት እንደነዚህ አይነት ክስተቶች ከሰውሰራሽ እና ከተጠቀሰው ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች እንደማይወጣ ግን አስረድተዋል፡፡

ምስል Andrea Danti/Zoonar/picture alliance

መሰል ክስተቶች በዓለም ዙሪያ በየጊዜው ተደጋግመው የሚስተዋሉና በብዛት ሰዎች በማይኖሩባቸው ባህርና በተለያዩ የምድር አካላት እንደሚወድቁም ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡ እነዚህ ባዕድ ነገሮች ወደ ምድር ላይ ደርሰው ስወድቁ መጠናቸው ከጥቃቅን የአሸዋ ስብርባሪ መጠን እስከ 100ሜትር ስፋት ልኖራቸው የሚችል ግዙፍ ሊሆኑም እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ ባዕድ ነገሮቹ ከተፈጥሮ መዘውራቸው በመውጣት ወደ መሬት ስወድቁ ምን ምክንትስ ይኖር ይሆን ተባሉት የስነህዋ ተመራማሪው፤ “ስነህዋ ምርምር እንደሚያሳየው በጣም ራቅ ያለ ቦታ ላይ የኮከቦች ወይም ጋላክሲዎች መጋጨትና ፍትጊያ ልኖር ይችላል” በማለት ይህ ፍትጊያ ከመስመራቸው በማውጣት መድርን ጨምሮ በተለያዩ ፕላኔቶች ላይ ልወድቁ እንደምችሉ አስረድተዋል፡፡

የህንድ የጠፈር ምርምር ግስጋሴ

ትናንት በደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል በስፋት በሰማይ ላይ የታየው የሚቀጣጠል ነገር እስካሁን ምድር ላይ ለመውደቁ የተገኘ ማስረጃ አለመኖሩን የገለጹት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የስነከባቢ አየር ተመራማሪው ዶ/ር ገመቹ ፋንታ፤ ለዚህ የህብረተሰቡ ጥቆማ እንደሚያሻቸው ገልጸዋል፡፡ ባለሙያው ተቀጣጣይ ነገሩ ሰማይ ላይ ሳይበታተን ወደ ምድር በሚወድቅበት አጋጣሚ ጉዳትም ሊያደርስ እንደሚችል በማስጠንቀቅ ማህበረሰቡ ባዕድ ተቀጣጣይ ነገሩ ሰው ወዳለበት ስፍራ የሚወድቅ ከሆነ መሸሽ እንደሚስፈልግም ጠቁመዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW