በኢትዮጵያ ጉዳይ የአውሮጳ ሕብረት መወያየቱ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 9 2014![USA New York | Pressekonferenz Josep Borrell](https://static.dw.com/image/59247837_800.webp)
ማስታወቂያ
የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትናንት መወያየታቸው ተሰምቷል። የሕብረቱ አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባካሄዱት ስብሰባ ከዚህ ቀደም የተለየ ውሳኔ እንዳላሳለፉ ከብራስልስ ዘጋቢያችን በላከልን ዜና ጠቅሷል። ባለፈው ጥቅምት ወር ማለቂያ በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በአውሮጳ ሕብረት ልዩ ልዩ ስብሰባዎች ከዋና መነጋገሪያዎች አንዷ ሆናለች።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ