1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆምና የሽግግር ጊዜ እንዲመቻች የቀረበ ጥሪ

ዓርብ፣ ነሐሴ 23 2017

በኢትዮጵያ በዘር ላይ የተመሰረተ ያለው ፖለቲካና የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም፣በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ትብብር ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ። የንቅናቅው ሊቀመንበር ዶክተር ባደገ ቢሻው ለዶቼ ቬለ እንዳሉት፣በሀገሪቱ ሁኔታዎች እየተረጋጉ ሲሄዱም ፍትህና ዲሞክራሲ የሚሰፍንበት የሽግግር ሂደት መፈጠር አለበት።

በኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆምና የሽግግር ጊዜ እንዲመቻች ጥሪ ቀረበ
በኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆምና የሽግግር ጊዜ እንዲመቻች ጥሪ ቀረበ ምስል፦ AMANUEL SILESHI AFP via Getty Images

በኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቀርብ በዲያስፖራ ማህበረሰብ የቀረበ ጥሪ

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆምና የሽግግር ጊዜ እንዲመቻች የቀረበ ጥሪ


በኢትዮጵያ በዘር ላይ የተመሰረተ ያለው ፖለቲካና የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም፣በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ  ትብብር ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ። 

የንቅናቅው ሊቀመንበር ዶክተር ባደገ ቢሻው ለዶቼ ቬለ እንዳሉት፣በሀገሪቱ ሁኔታዎች እየተረጋጉ ሲሄዱም ፍትህና ዲሞክራሲ የሚሰፍንበት የሽግግር ሂደት  መፈጠር አለበት። 

ስለጉዳዮ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው፣የፖለቲካ ተንታኝ አያና ፈይሳ በበኩላቸው፣የሽግግር መንግሥት ከመመስረት ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ  የመፍትሔ ዐሳቦችን የኢትዮጵያ መንግስት ተቀብሎ ለመፈፀም የሚቸግርባቸው እንደሆኑ አመልክተዋል። 

 

የኢትዮጵያውያን የትብብር ንቅናቄ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚመክር የበይነ መረብ ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት፣ጉባኤተኞቹ አገሪቱ በየመስኩ እያሽቆለቆለች እንደመጣች መተማመን ላይ መድረሳቸውን የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶክተር ባደገ ተናግረዋል። 

እንዲሁም፤የአካባቢውን ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ እና የኀይል አሰላለፍ በመዳሰስ፣ከመቼውም ጊዜ በላይ አገሪቱ ትልቅ ውጥረት ውስጥ እንደምትገኝ መምከራቸውን ሊቀመንበሩ አመልክተዋል።

 

ኢትዮጽያ ከየት ወዴት?

''የሀገራችን ሁኔታ፣የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና የማኀበራዊ ሁኔታው ከምጊዜውም በላይ እየከፋ በመሄዱ፣ምን ብናደርግ ይሻላል በሚል ነው የተነሳሳነው እና በእዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ከየት ወዴት እየሄድን ነው የሚል ጥያቄ ነው ራሳችንን የጠየቅነው ፤እና በዚህ ላይ የታወቁ ምሁራንና  ፖለቲከኞችን ጋብዘን ዐሳባቸውን እንዲሰጡን ከዚያም ደግሞ ከዚህ ችግር እንዴት እንወጣለን በሚል የተዘጋጀ ኮንፈረንስ  ነው። ''

የኢትዮጵያውያን የትብብር ንቅናቄ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚመክር የበይነ መረብ ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት፣ጉባኤተኞቹ አገሪቱ በየመስኩ እያሽቆለቆለች እንደመጣች መተማመን ላይ መድረሳቸውን የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶክተር ባደገ ተናግረዋል። ምስል፦ Dr. Badege Bishaw

ጉባኤተኞቹ በመፍትሔ ዐሳብነት ካቀረባቸው ጉዳዮች ዋነኛውም፣በሀገሪቱ ሰፍኗል ያሉት የዘር ፖለቲካ እና የሚካሄደው ጦርነትም  እንዲቆም የቀረበው ጥሪ ነው ይላሉ ሊቀመንበሩ። 

‘’ከዚህ ከዘር ፖለቲካ ፈጥነን መውጣት አለብን፣ይሄ ነገር በኢትዮጵያ ላይ ከቆየ ትልቅ እርስ በርስ ጦርነት ሊያመጣ ይችላል። ስለዚህ ቶሎ አገሪቷ ከመፍረሷ በፊት፣ይሄ ጦርነት እና የዘር ፖለቲካ መቆም አለበት። ''

 

የሽግግር ሂደት አስፈላጊነት 

በማስከተልም፣ፍትሕና ዴሞክራሲ የሚሰፍንበት የሽግግር ሂደትመመቻቸት እንደሚገባው ዶክተር ባደገ አመልክተዋል። 

ጉባኤተኞቹ ያቀረባቸውን የመፍትሄ ዐሳቦች እንዴት ገቢራዊ ለማድረግ እንደታሰበ ጥያቄ ያቀረብንላቸው ሊቀመንበሩ፣ሕዝቡ ነፃነቱንና መብቱን ለማስጠበቅ ድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባው አሳስበዋል። 

ከዚህ አኳያ ዜጎች መብታቸውን የሚያስከብሩበት፣ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አስፈላጊነት በጉባኤው ታምኖበታል ብለዋል። 

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ዶቼ  ቬለ የጠየቃቸው፣የፓለቲካ ተንታኝ አያና ፈይሳ በበኩላቸው፣በውጪ የሚገኙ ትብብሮች ዋና አላማ የመንግስትን ስልጣን፣በሽግግር ጊዜ ስም ለመረከብ ነው ባይ ናቸው። ምስል፦ Ayana Feyissa

 

የፓለቲካ ተንታኝ አስተያየት 

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ዶቼ  ቬለ የጠየቃቸው፣የፓለቲካ ተንታኝ አያና ፈይሳ በበኩላቸው፣በውጪ የሚገኙ ትብብሮች ዋና አላማ የመንግስትን ስልጣን፣በሽግግር ጊዜ ስም ለመረከብ ነው ባይ ናቸው። 

‘’የእነዚህ ትብብሮች ዋነኛ ዓላማቸው ፣የመንግሥትን ሥልጣን እኛ የምንይዝበት መንገድ፣ደግሞ ክፍተት ሲፈጠር እኛየሽግግር መንግሥት ሆነን የምንመጣበትን መንገድ ስለማመቻቸትና እዛ ላይ ስለመስማማት የሚል ነው። ስለዚህ ለእዛ የሚያመቹ ሁኔታዎች ብቻ እንደሚያዩ ያስታውቃል።''

መንግስት፣ከእነዚህ ወገኖች፣ከሽግግር መንግስት ምስረታ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ምክር ሀሳቦችን እንደ በጎ  መፍትሔ ለመቀበል ይቸግራል ብለው እንደሚያምኑም አቶ አያና አብራርተዋል። 

'' እነርሱ በእርሱ ፈንታ እንዴት አድርገው የሽግግር  መንግስት እንደሚመሠረቱ፣እርሱ ላይ ያጠነጠነ ነው። ነገሮችን ችግሮችን መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችም የሚታዩት፣በእዛ ዐይንና መነጽር ብቻ ስለሆነ ተቀብሎ፣ለማስፈፀም የሚያስቸግር ነው። የችግሮች ትንትናቸውም፣የመፍትሔ ጥቅማቸውም ከዚሁ ጋር የተያያዘ  ስለሚሆን ክፍተት ይኖረዋል ማለት ነው። ''ብለዋል።
ታሪኩ ሃይሉ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW