1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮ ሱዳን ድንበር አካባቢ ያሉ ስደተኞች ስሞታ

ቅዳሜ፣ መስከረም 4 2017

አንዲት በምጥ ላይ የነበረች እናት የሁለቱን ድንበር እንድትሻገር ከተፈቀደላት በኋላ ገላባት ብትደርስም የደም እጥረት በማጋጠሙና ቶሎ ወደ ህክምና ቦታው ባለመድረሷ ህይወቷ ማለፉን ዳውድ የተባለ ስደተኛ ተናግሯል፡፡

የሱዳን ስደተኞች መጠለያ በከፊል
የሱዳን ስደተኞች መጠለያ በከፊልምስል UNCHCR

በኢትዮ ሱዳን ድንበር አካባቢ ያሉ ስደተኞች ስሞታ

This browser does not support the audio element.

ከሱዳን ተፈናቅለው ከስደተኛ ጣቢያ የወጡና በኢትዮ ሱዳን ድንበር አካባቢ ያሉ ስደተኞች ለምግብ፣ ለውሀና ለመድኃኒት እጥረት መጋለጣቸውን አመለከቱ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ደግሞ አካባቢው ሲረጋጋ እርዳታ እንደሚያደርስ አስታውቋል፡፡
በሱዳንና ኢትዮጵያ አዋሳኝ ድንበር ላይ የሚገኙ ስደተኞች ባለፈው ሳምንት በፋኖና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መካከል ሲካሄድ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮ ሱዳን ድንበር በመዘጋቱ ወደ አካባቢውተንቀሳቅሶ ሸቀጦችን ለመግዛት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡
ከስደተኞች አብደላ የተባለ ስደተኛ እንዳለው መንገዱ በመዘጋቱ ወደ ገላባት ተንቀሳቅሶ ግብይት ለማድረግ አልተቻለም በኢትዮጰያ መተማ አካባቢ ግዥ ለማከናወንም የገንዘብ እጥረት አጋጥሞናል ብሏል፡፡
የውሀ፣ የምግብና የመድኃኒት እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ስደተኛውን እየፈተነው እንደሆነ ሌላ ስደተኛ አመልክቷል፡፡
አንዲት በምጥ ላይ የነበረች እናት የሁለቱን ድንበር እንድትሻገር ከተፈቀደላት በኋላ ገላባት ብትደርስም የደም እጥረት በማጋጠሙና ቶሎ ወደ ህክምና ቦታው ባለመድረሷ ህይወቷ ማለፉን ዳውድ የተባለ ስደተኛ ተናግሯል፡፡
ተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽንበደብዳቤ ለዶቼ ቬሌ እንደገለፀው፣ የፀጥታው ሁኔታ እስከፈቀደ ድረስ የሁለቱ አገሮችን በሚያዋስነው (Transit center) ለሚገኙ ስደተኞች ምግብና ውሀ ለማቅረብ አቅዷል፡፡
ሁለቱን አገሮች በሚያዋስነው መግቢያ በር አካባቢ ወደ ስደተኛ መጠለያ አንገባም ያሉ ከ1500 በላይ የሱዳን ስደተኞች ይገኛሉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ወደ መጠለያ ለመግባት  ፈቃደኛ ያልሆኑ 800 ስደተኞች ወደ ኢትዮ ሱዳን ድንበር መሄዳቸውን አረጋግጧል። ሱዳን አሁን ጦርነት በመኖሩ ስደተኞች ወደዚያ እንዲሄዱ ድርጅቱ አያበረታታም፣ ድጋፍና እገዛም አያደርግም ብሏል የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በምዕራብ ጎንደር  ዞን መተማ ወረዳ የሚገኙትን ኩመርና አውላላ የተባሉ ሁለት የስደተኞች ጣቢያዎችን  በተለያዩ ምክንትች ዘግቶ አፍጥጥ ወደተባለ አዲስ መጠለያ አስገንብቶ ፈቃደኛ የሆኑ  ስደተኞችን ወደዚያ ማዛወሩ መዘገቡ ታወሳል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን  የሐምሌ 2024 ሪፖርት እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን 64 ሺህ 412 የተለያዩ አገር ስደተኞች በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በሚገኙ 24 የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ይኖራሉ። ከ4 ሚሊዮን በላይ ደግሞ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ደግሞ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተመዝግበዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW