1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኢኳቶሪያል ጊኒ ማርቡርግ ተህዋሲ ያሳደረገዉ ስጋት

ማክሰኞ፣ የካቲት 7 2015

በኢኳቶሪያል ጊኒ ማርቡርግ በተባለ በጣም አደገኛ እና ተዛማች ተህዋሲ የተለከፉ ሰዎች መገኘታቸዉ ተገለፀ። የዓለም የጤና ድርጅት እንዳስታወቀዉ በበሽታው ከተለከፉ ሰዎች መካከል እስካሁን ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል። የኢኳቶሪያል ጊኒ መንግስት በሽታዉ በተዛመተባቸዉ አካባቢዎች ላይ «የጤና ማስጠንቀቂያ» አዋጅ ደንግጓል።

Marburg-Virus
ምስል፦ CDC/dpa/picture alliance

በኢኳቶሪያል ጊኒ ማርቡርግ በተባለ በጣም አደገኛ እና ተዛማች ተህዋሲ የተለከፉ ሰዎች መገኘታቸዉ ተገለፀ።  የዓለም የጤና ድርጅት እንዳስታወቀዉ በበሽታው ከተለከፉ ሰዎች መካከል እስካሁን ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል። ከሰሃራ በታች በምትገኘዉ የአፍሪቃዊትዋ ሃገር ኢኳቶሪያል ጊኒ መንግስት በሽታዉ በተዛመተባቸዉ አካባቢዎች ላይ «የጤና ማስጠንቀቂያ» አዋጅ ደንግጓል። የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከ4,000 የሚበልጡ ሰዎች በተገለለ ስፍራ እንዲዎቆዩ መደረጉንም ገልጿል። ማርቡርግ በተባለዉ አደገኛ ተህዋሲ የመያዝ ዋንኛ ምልክቶች  ከፍተኛ ትኩሳት፣ የደም ተቅማጥ፣ ድካምና ከባድ ራስ ምታት እንደሆነም ተያይዞ ተገልጿል። እንደ ዓለሙ የጤና ድርጅት ከሆነ በማርቡርግ ተህዋሲ የተያዘ ሰዉ የመሞት እጣዉ 88 በመቶ ነው። የማርቡርግ ተህዋሲ በጎርጎረሳዉያኑ 1967 ዓ.ም በጀርመንዋ ሄሰን ግዛት በማርቡርግ ከተማ የመድኃኒት ኩባንያ ቤተ ሙከራ ከዩጋንዳ በመጡ የሙከራ ጦጣዎች ላይ በመገኘቱ ተህዋሲዉ የከተማዋን ስም መያዙ ተመልክቷል።

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW