1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኤሌክትሪክ ኃይል እጥረትና በዋጋዉ ንረት ምክንያት ፋብሪካዎች እየከሰሩ ነዉ

ኢሳያስ ገላው
ዓርብ፣ ነሐሴ 16 2017

ኮምቦልቻ የተለያዩ ፋብሪካዎች የሚገኙባት የኢንዱስትሪ ከተማ ናት።የፋብሪካዎቹ ባለቤቶች እንደሚሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ የኤሌክትሪክ ኃይል በተደጋጋሚ በመቆራረጡ ከሥራ ለመዉጣት እየተገደዱ ነዉ።ሠራተኞች በበኩላቸዉ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ አነስተኛ አምራቾችንም መጉዳቱን ይናገራሉ

(ፎቶ ከክምችታችን) ደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ከሚገኙ ፋብሪካዎች አንዱ-በከፊል።የኢንዱስትሪ ከተማ በሆነችዉ ኮምቦልቻ ከተማ የሚሠሩ ፋብሪካዎች በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ሥራ ለማቆም እየተገደዱ መሆኑን ባለቤቶቹ ይናገራሉ።
(ፎቶ ከክምችታችን) ደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ከሚገኙ ፋብሪካዎች አንዱ-በከፊል።የኢንዱስትሪ ከተማ በሆነችዉ ኮምቦልቻ ከተማ የሚሠሩ ፋብሪካዎች በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ሥራ ለማቆም እየተገደዱ መሆኑን ባለቤቶቹ ይናገራሉ።ምስል፦ picture-alliance/dpa

በኤሌክትሪክ ኃይል እጥረትና በዋጋዉ ንረት ምክንያት ፋብሪካዎች እየከሰሩ ነዉ

This browser does not support the audio element.

ኮምቦልቻ-ደቡብ ወሎ የሚገኙ የፋብሪካ ባለቤቶች በኤልክትሪክ ኃይል እጥረትና በየጊዜዉ በሚንረዉ የኃይል ዋጋ ምክንያት ፋብሪካዎቻቸዉ እየከሠሩ መሆኑን አስታወቁ።ኮምቦልቻ የተለያዩ ፋብሪካዎች የሚገኙባት የኢንዱስትሪ ከተማ ናት።የፋብሪካዎቹ ባለቤቶች እንደሚሉት ከቅርብ ጊዜ  ወዲሕ የኤሌክትሪክ ኃይል በተደጋጋሚ በመቆራረጡ ከሥራ ለመዉጣት እየተገደዱ ነዉ።ሠራተኞች በበኩላቸዉ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ አነስተኛ አምራቾችንም መጉዳቱን  ይናገራሉ

የኤሌትሪክ ሀይል ለወራት እየተቆራረጠፋብሪካዎቻቸው ከሚያመርቱበት ቀን ይልቅ ያለምርት የሚያሳልፉበት ሰራተኞቻቸው ያለስራ ደመወዝ የሚከፈልባቸው በአማራ ክልል የኢንድስትሪ መዳረሻ የሆነችው ኮምቦልቻ ከተማ እና በዙሪያው ያሉ ፋብሪካ ባለቤቶች አሁን ያለው ሁኔታ ፈትኖናል አሉ፡፡ ‹‹አሁን ግቢ ውስጥ ሔደህ ሰራተኞችን ብታይልኝ ምንም እየሰራን አይደለም፤ ለህዝብ ተደራሽ አልሆንም፤ ምርት እያለን እቃ እያለን፤ መፍጨት አቃተን፤ ሰራተኛ ቁጭ ብሎ ደመወዝ እየከፈልን ነው፡፡›› 

በመብራት ሀይል መቆራረጥ ምክንያት ፋብሪካ መዝጋት ማሰብ

የመብራት ሀይል መቆራረጡ ከፍተኛ በመሆኑ ፋብሪካ ለመዝጋት እስከ ማሰብ ያደርሳል የሚሉት የፋብሪካ ባለቤቶች መቆራረጡ እንዳለ ሆኖ እንኳን ለመስራት፤ መብራት ከሚኖርበት የማይኖርበት ጊዜ ይበዛል ሲሉ ይናገራሉ፡፡ 

‹‹ያለው ችግር በጣም ከፍተኛ ነው፤ ከምንሰራበት የማንሰራበት ነው የሚበልጠው እና ከአቅም በላይ ሆኗል እየሰራን አይደለም፤ ለመዝጋት የሚያስችል ነው ያለው ሁኔታ ስራ አያስቀጥልም፤ የሚበራበትን ጊዜ ብትጠይቀኝ ነው የሚሻለኝ፡፡›› 

ችግሩ ከከፍተኛ ፋብሪካዎች በዘለለም በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተደራጅተው የሚሰሩ አምራቾች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የሚናገሩት የስራ አንቀሳቃሾች ያለ ስራ ለሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል ተገደናል ሲሉ ይገልፃሉ፡፡ 

‹‹በጣም ጎድቶናል ይቆራረጣል፤ ለአንድ ቀን ሙሉ የሚቋረጥበት ጊዜ አለ፣ አልፎ አልፎ የሚቆራረጠው ብቻ ሳይሆን ማምረት ላይ በብዙ ይጎዳል ዝም ብለን ለሰራተኛ የምንከፍለው፡፡›› 

ሰራተኞች ለመቀነስ ማሰብ

አሁን ላይ ሰራተኞችን ለመቀነስ እያጤንን እንገኛለን የሚሉት ባለሀብቶች ከመብራት በተጨማሪ የውሃ እጥረት ስራውን አስተጓጉሎታል ይላሉ፡፡ 

‹‹አሁን ላይ ያለን አማራጭ ሰራተኞቻችንን እንዴት እናድርግ  ነው፤ አሁን የመብራቱን ስላያችሁት ነው በእያንዳንዱ ቤት ስለሚጠፋ፤ ውሃም እንደዚሁ ነው የሚጫወትብን፤ ሆን ብለውም ሊሆን ይችላል የመልካም አስተዳደርም ችግር ይመስላል፡፡›› 

የመብራት መቆራረጡ ለወራት እንደዘለቀ የሚገልፁት በአነስተኛ የልብስ ስፌት ስራ ላይ የተሰማሩ ስራ ፈጣሪዎችን መቆራረጡ በመቀጠሉ ቤተሰቦቻችንን ለመመገብ አልቻልንም በማለት ይናገራሉ፡፡ 

‹‹አብዝሃኛው ማህበረሰብ በቀን ስራ የሚተዳደር ነው ቀኑን ሙሉ መብራት ከሌለ እኛ የምንበላው የለም፡፡ የምናገኘው ነገር የለን፤ ይህ በተደጋጋሚ ለወራት የቆየ ነው በዚህ ሁኔታ ላይ ይህ ማህበረሰብ እንዴት ነው ሰርቶ መብላት የምንችለው፡፡›› 

(ፎቶ ከክምችታችን) ደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ከሚገኙ ፋብሪካዎች አንዱ-በከፊል።የኢንዱስትሪ ከተማ በሆነችዉ ኮምቦልቻ ከተማ የሚሠሩ ፋብሪካዎች በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ሥራ ለማቆም እየተገደዱ መሆኑን ባለቤቶቹ ይናገራሉ።ምስል፦ picture-alliance/dpa

በስድስት ከተሞች የሚሰራ የመብራት ፕሮጀክት አለመጠናቀቅ

በኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ሀይል ደሴ ሪጅን ዳይሬክተርአቶ ሀብቱ አበበ እንደሚገልፁግትም አሁን በኮምቦልቻ ደሴ እና የተለያዩ አካባቢ የተፈጠረው የሀይል መቆራረጥ በ6 ከተሞች ላይ በሚሰራ ፕሮጀክት ምክንያት የመጣ በመሆኑ  ፕሮጀክቱን በፍጥነት አጠናቀን ወደቀደመ የሀይል ስርጭት እንመለሳለን ይላሉ፡፡

‹‹ትንሽ ችግሩን ያባባሰው የ6 ከተሞች ፕሮጀክት እየተሰራ በመሆኑ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በባለፈው የጀመረው ያላጠናቀቀው ምሰሶውን አቁሞ ሽቦ ያልተዘረጋ ከነባሩ መስመር ጋር ስለተጠጋጋ ኮንክሪቱ ጋር ሲጋጭ ነው ሀይል እያጠፋብን ያለው፡፡ ፕሮጀክቱን ቶሎ እንዲጠናቀቅ ተነጋግረናል፡፡ እሱ ከጨረሰ ይስተካከላል፡፡ 
ለተወሰነ ሰዓታት ለ8፡00 እና 9፡00 ሰዓት ሀይል ያጠፋሉ ስራውን ለመስራት እና በአጭር ጊዜ አጠናቁ ተብሏል፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይስተካከላል፡፡›› 

በኮምቦልቻ ከተማ 3 ሰብስቲቲዩሽን ያሉ በመሀኑ ምንም አይት የሀይል እጥረት አለጋጠመንም የሚሉት አቶ ሀብቱ አበበ የቀደሙት የመብራት ሀይል አስተላላፊ መስመሮችን በአዲስ የመተካት ስራው ሲጠናቀቅ አስተማማኝ የሀይል አቅርቦት ይኖረናል ብለዋል፡፡

ኢሳያስ ገላዉ

ነጋሽ መሐመድ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW