1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኤርትራ ማዕቀብ መነሳት እነማን ሚና ነበራቸው ?

ረቡዕ፣ ኅዳር 5 2011

የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ለዘጠኝ ዓመት ጥሎት የቆየውን ማዕቀብ ዛሬ አንስቷል።  ምክር ቤቱ የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እና የጉዞ እና የንብረት እግድን አስመልክቶ ኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ብሪታንያ ያረቀቀችውን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ ደግፏል።

UN-Sicherheitsrat in New York | Debatte Sanktionen gegen Eritrea
ምስል picture-alliance/Xinhua News Agency/L. Muzi

በኤርትራ ማዕቀብ መነሳት እነማን ሚና ነበራቸው ?

This browser does not support the audio element.

የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታዉ ምክርቤት የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በኤርትራ ላይ ማዕቀቡን ያሳረፈዉ፤ ኤርትራ በጎረቤት ሶማልያ የሚንቀሳቀሰዉን የደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብን ትረዳለች በሚል እና ኤርትራ ከጅቡቲ ጋራ ያላትን የድንበር ዉጥግብ ለመፍታት ጥረት አላደረገችም በሚል ነበር ። ማዕቀቡ የጦር መሳርያና ግዥ ማዕቀብንና፤ ባለሥልጣናት ወደ ዉጭ ሃገር እንዳይጓዙ የሚከለክል እንዲሁም በዉጭ ሃገራት የሚገኝ ሃብታቸዉ እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርግ ነዉ።

የማዕቀቡን መነሳት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ለኤርትራ ህዝብና መንግስት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል። በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አማካኝነት የተላለፈው መግለጫ የማዕቀቡ መነሳት በአፍሪቃ ቀንድ ለሚታየው መረጋጋት እና ሰላም ዘለቄታዊነት ብሎም በቀጠናው ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብሏል።  

ከውሳኔው መተላለፍ አስቀድሞ የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ አንድ የኢትዮጵያ የቀድሞ ዲፕሎማት እንዲሁም የማኅበራዊ ሳይንስ ባለሞያን አነጋግሮ ነበር። ማዕቀቡ እንደሚነሳ ቅድሚያ ግምታቸውን ሰጥተው የነበሩት ሁለቱ የፖለቲካ ታዛቢዎች ለዚህም ምክንያቶች ናቸው ያሏቸውን አብራርተዋል። 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።   

 

መክብብ ሸዋ

ተስፋለም ወልደየስ

ነጋሽ መሐመድ 


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW