በአዲስ አበባ የኤርትራ ኤምባሲ ዳግም ተከፍቷል
ሰኞ፣ ሐምሌ 9 2010![Äthiopien Eritrea eröffnet Botschaft beim einstigen Kriegsgegner](https://static.dw.com/image/44700418_800.webp)
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦር ከተማዘዙ ወዲህ ተዘግቶ የነበረው የኤርትራ ኤምባሲ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አወርቂ በተገኙበት እንደገና በይፋ ተከፍቷል። በመክፈቻው ሥነ-ስርዓት ላይ የኤርትራ ባንዲራ ዳግም በኤምባሲው የተውለበለበ ሲሆን የሀገሪቱ ብሔራዊ መዝሙርም ተዘምሯል። በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አጠገብ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ቅጽር ግቢ ለበርካታ ዓመታት ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን እንዲገለገልበት ተፈቅዶለት ይጠቀምበት እንደነበር ይታወሳል።
በዚሁ በኤርትራ ኤምባሲ ዳግም መከፈት ላይ አራማጆች (አክቲቪስቶች) ሀሳባቸውን ለዶይቼ ቬለ አካፍለዋል። አስተያየቶቹን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ተስፋለም ወልደየስ
አዜብ ታደሰ