በኤች አይ ቪ ላይ አተኩረዉ የሚሰሩ ድርጅቶች ጥምረት
ሐሙስ፣ ሰኔ 16 2003ማስታወቂያ
ከአንድ መቶ በላይ እንደሆኑ የተገለጸዉ እነዚህ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥምረቱን የፈጠሩት በቫይረሱ ላይ የከፈቱትን ዘመቻ በጋራ አጠናክረዉ ለመቀጠል እንደሆነ ተገልጿል። ይህ አዲሱ ስልት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በተናጠል የሚደረገዉን ጥረት በአንድነት በማምጣት በተጠናከረ መርሃግብር አማካኝነት ዘመቻዉን ለማካሄድ እንደሚጠቅም ተመልክቷል። በዚህ ጥረትና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶችም የቫይረሱ ስርጭት የመቀነስ አዝማሚያ ማሳየቱ ነዉ የተገለጸዉ።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ