1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በእስራኤል ጦር ኃይል አባላት ላይ የቀረበ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ወቀሳ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 9 2001

የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ ባካሄደው ሶስት ሳምንታት በቆየው የጥቃት ዘመቻው ወቅት ወታደሮቹ በሲቭሉ የፍልስጤም ህዝብ አንጻር ኢሰብዓዊ ድርጊት ፈጽመዋል ሲል አንድ ራሱን ዝምታን ማብቃት ብሎ የሚጠራመንግስታዊ ያልሆነው የእስራኤል ድርጅት ባወጣው ዘገባ ወቀሳ አሰማ።

ምስል AP

ድርጅቱ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ከሰላሳ የሚበልጡ የእስራኤል ጦር አባላትን መረጃ ጠቅሶ ነው ዘገባውን ያወጣው። የእስራኤል መከላከያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሞራል ስርዓት አለው የሚሉ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ድርጊቱ በግለሰቦች ደረጃ እንጂ የመከላከያ መመሪያን ተከትሎ የተወሰደ አልነበረም በማለት ወቀሳውን አስተባብለዋል። በሶስት ሳምንቱ የጋዛ ጦርነት ከአንድ ሺህ አራት መቶ የሚበልጡ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ፡ ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ቆስለዋል።

እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ ፈጸመችው የተባለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ

ዜናነህ መኮንን/አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW