1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በእስቴ የተቃጠሉ መስጊዶችን ለመስራት ያገጠመ ችግር

ረቡዕ፣ ጥር 27 2012

ባለፈዉ ዓመት በእስቴ ከተማ ቃጠሎ የደረሰባቸዉን መስጊዶችን መልሶ ለመገንባት የገንዘብ እጥረት ማጋጠሙ ተገለፀ። ከዓመት በፊት በአማራ ክልል፣ ደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ መካነየሱስ ከተማ በተቀሰቀሰ ሁከት ቃጠሎ የደረሰባቸዉን መስጊዶች መልሶ ለመገንባት የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው አሰሪ ኮሚቴው ገለፀ።

Äthiopien | Wiederaufbau Moschee in South Gonder
ምስል DW/A. Mekonnen

ለመልሶ ግንባታዉ ገንዘብ ለመስጠት ቃል የገቡ በርካታ ቢሆንም ቃሉን የጠበቀ ግን የለም

This browser does not support the audio element.

ቃጠሎውን ተከትሎ መስጊዶቹን መልሶ ለመገንባትና ለአገልግሎት ለማብቃት በረካታ ሰዎችና ተቋማት ቃል የገቡ ቢሆንም፤ እስካሁን ቃሉን ጠብቆ ገንዘብ ገቢ ያደረገ አካል ባለመኖሩ፤ ግንባታው የታሰበውን ያህል አንዳልሄደና በአሁኑ ወቅት በገንዘብ እጥረት ስራውን እስከማቆም መድረሳቸውን የአሰሪ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ ሀጂ ኡስማን አሊ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።
 ነዋሪዎች በበኩላቸዉ በተፈጠረዉ የገንዘብ እጥረት እስካሁን የመስጊዱን መሰረት ለመጣል እንኳ ችግር ማጋጠሙን ገልፀዋል። ባለፈው አንድ ዓመት ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖች ባደረጉት ድጋፍ የመስጊዶቹን መሰረት የመጣል ስራ ለመስራት እየተሞከረ ቢሆንም የመሬቱ ተፈጥሯዊ ሁኔታ አስቸጋሪ በመሆኑ በተገኜዉ ዉሱን ገንዘብ ማጠናቀቅ አለመቻሉን የአሰሪ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ ሀጂ ኡስማን አሊ ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል፡፡ስለሆነም «በቀጣይ የአገሪቱ የሰላም ሁኔታ የተረጋጋና አስተማማኝ ከሆነ ተንቀሳቅሰን ገንዘብ በማሰባሰብ መሰጊዶቹ አንዲገነቡ አናደርጋለን» ብለዋል፡፡ ሁለቱ መስጊዶች የዛሬ ዓመት ጥር 26/2011 ዓ ም በአማራ ክልል፣ ደቡብ ጎንደር ዞን፣ እስቴ ወረዳ፣ መካነየሱስ ከተማ በተነሳ ሁከት ነበር ለቃጠሎ የተዳረጉት።

ምስል DW/A. Mekonnen


ዓለምነዉ መኮንን


ፀሐይ ጫኔ
አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW