1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በእነ ጀዋር መሐመድ ላይ ምስክር ሊሰማ የነበረው ችሎት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ

ሰኞ፣ ጥቅምት 22 2014

በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ የክስ መዝገብ ስር የተጠቀሱ 24 ተከሳሾች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ቃል ለመስማት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ለዛሬ ሰጥቶ የነበረው የችሎት ቀጠሮ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ።

Äthiopien Jawar Mohammed
ምስል Tiksa Negeri/Reuters

በእነ ጀዋር መሐመድ ላይ ምስክር ሊሰማ ተይዞ የነበረው ቀጠሮ ተላለፈ

This browser does not support the audio element.

በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ የክስ መዝገብ ስር የተጠቀሱ 24 ተከሳሾች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ቃል ለመስማት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ለዛሬ ሰጥቶ የነበረው የችሎት ቀጠሮ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ።

ችሎቱ ከተሰየመ የምስክር አሰማም ሂደቱ ያልተጀመረው በክስ ሂደቱ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የተከሳሾች ጠበቆች በየፊናቸው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቃቸውን ተከትሎ መዝገቡ በመታገዱ ነው ተብሏል፡፡

ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለዛሬ ይዞ በነበረው ችሎት አቶ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሃምዛ አዳኔ እና አቶ ደጀነ ጣፋ በሌሉበት በግልጽ ችሎት የምስክሮችን ለመስማት   ነበር ቀጠሮው ይዞ የነበረው፡፡

ይሁንና የተከሳሾች ጠበቆች አራቱ ተከሳሾች በሌሉበት የምስክር የመስማት ሂደቱ መጀመር የለበትም በሚል እና አቃቤ ህግ በበኩሉ ችሎቱ የምስክሮቹን ቃል ከመጋረጃ ጀርባ መቀበል አለበት በማለት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤት ማለታቸውን ከጠበቆቹ አንዱ አቶ ቱሊ ባይሳ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

ስዩም ጌቱ 

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW