1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮሚያ ክልል ለሚፈፀም ግድያና እስራት የባለስልጣናት ትዕዛዝ አለበት መባሉ

ዓርብ፣ የካቲት 15 2016

በኦሮሚያ ክልል ለሚፈፀም ከሕግ ውጭ ግድያና እስራት የባለስልጣናት ሚስጥራዊ ኮሚቴ ትዕዛዝ ሲሰጥ መቆየቱን ሮይተርስ የዜና ወኪል ገለፀ። በኢትዮጵያ የከፍተኛ ባለሥልጣናት የሚስጥራዊ ኮሚቴ፣ብዙ ህዝብ በሚኖርበት የኦሮሚያ ክልል፤ አማጽያንን ለመደምሰስ በሚል ከሕግ አግባብ ውጭ ግድያና ሕገወጥ እስራት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተዘግቧል።

ፎቶ ማህደር፤ ኦሮምያ ክልል
ፎቶ ማህደር፤ ኦሮምያ ክልል ምስል Seyoum Getu/DW

በኦሮሚያ ክልል ለሚፈፀም ከሕግ  ውጭ ግድያ እና  እስራት የባለስልጣናት  ትዕዛዝ አለበት መባሉ 


በኦሮሚያ ክልል ለሚፈፀም ከሕግ  ውጭ ግድያ እና  እስራት የባለስልጣናት ሚስጥራዊ ኮሚቴ ትዕዛዝ ሲሰጥ መቆየቱን ሮይተርስ የዜና ወኪል ገለፀ። በኢትዮጵያ የከፍተኛ ባለሥልጣናት የሚስጥራዊ ኮሚቴ፣ብዙ ህዝብ በሚኖርበት የኦሮሚያ ክልል፤ አማጽያንን ለመደምሰስ በሚል ከሕግ አግባብ ውጭ ግድያ እና ሕገወጥ እስራት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ማስተላለፉን የሮይተርስ የምርመራ ግኝት አመልክቷል። ሮይተርስ በዚህ ምርመራው ከ30 በላይ የፌደራል እና የአካባቢ ባለስልጣናትን ፣ዳኞችን፣ጠበቆችን፣በባለሥልጣናት እና በደል የሚደርስባቸውን ሰለባዎች ማነጋገሩን ጠቁሟል። የዜና ምንጩ  በሀገር ውስጥ ፖለቲካ እና የፍትህ ባለስልጣናት የተነደፉ ሰነዶችንም መገምገሙንም አስታውቋል።ከእነዚህ ቃለ መጠይቆች እና ሰነዶችም በኦሮምኛ ቋንቋ «ኮሬ ነጌኛ»ወይም የደህንነት ኮሚቴ  የሚባለውን አካል አሠራርን ይፋ የሚያደርግ መረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱን የዜና ምንጩ ገልጿል።
-
እንደ ሮይተርስ የፀጥታ ኮሚቴው በኦሮምኛ ቋንቋ ፤«ኮሬ ነጌኛ» ሥራ የጀመረው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ከወራት በኋላ ሲሆን፤ከጎርጎሪያኑ 2018. ዓ/ም በፊት ግን ኮሚቴው አለመኖሩን ዘግቧል። አምስት የአሁን እና የቀድሞ የመንግስት ባለስልጣናት ነገሩኝ ብሎ ሮይተርስ እንዳሰፈረው፤ ይህ ኮሚቴ ዓላማው የራስን እድል በራስ ለመወሰን  ለዓመታት የዘለቀውን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ጦር  የሽምቅ ውጊያ እንዲያበቃ ማድረግ ነው። ከሮይተርስ  ከአምስቱ ምንጮች አንዱ የቀድሞ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሚልኬሳ ገመቹ  ሲሆኑ፤ እሳቸውን ጨምሮ አምስቱ ባለስልጣናት እንዳሉት ፤ በጎርጎሪያኑ 2019 ዓ/ም አዲስ የኦሮሞ ህዝብ አመፅ ሲቀሰቀስ ጠንከር ያለ እርምጃ በመውሰድ  ይህ ኮሚቴ የመሪነት ሚና  ነበረው። 

የኮሬ ነጌኛ እንቅስቃሴዎችን የሚያውቁ ሰዎች በኮሚቴው ትዕዛዝ በርካታ ግድያዎች ተፈጽመዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እስር ተካሂዷል ሲል ሮይተርስ ባወጣው ዝርዝር የምርመራ ዘገባ አመልክቷል።

ፀሀይ ጫኔ 

ኂሩት መለሰ 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW