1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በመንገደኞች ላይ የተፈጸመው ዕገታ እና አንድምታው

ሐሙስ፣ ነሐሴ 2 2016

ባለፈው ሳምንት ዓርብ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም አከባቢ በተፈጸመ የታጣቂዎች እገታ ከአንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ውስጥ በርካቶች ታግተው መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ፡፡ የፀጥታ ኃሎች በእለቱ ደርሰው በርካቶችን ብያስጥሉም ወደ አስር ሰዎች ግን እስካሁንም በአጋቾች እጅ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

Äthiopien I Keine Bewegung in der Region Oromia - Militante hatten vor jeder Bewegung gewarnt
ምስል Seyoum Getu/DW

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ታጣቂዎች በፈጸሙት ዕገታ 3 ሰዎች ተገደሉ

This browser does not support the audio element.

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ በመንገደኞች ላይ የተፈጸመ ሌላ እገታ

ባለፈው ሳምንት ዓርብ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም አከባቢ በተፈጸመ የታጣቂዎች እገታ ከአንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ውስጥ በርካቶች ታግተው መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ፡፡

አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣን በፊናቸው በታጣቂዎቹ በተፈጸመ የእገታ ተግባር አብዛኞቹን የፀጥታ ኃሎች በእለቱ ደርሰው ብያስጥሉም ወደ አስር ሰዎች ግን እስካሁንም ማስለቀቅ አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡

የታጋች ተማሪ ቤተሰቦች ጭንቀት

ለደህንነታቸው ስባል ስማቸውንም ሆነ ድምጻቸውን እንዳንጠቀም ተምጽነው አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ የአከባቢው ነዋሪ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ፊቼ እና ገርባጉራቻ ከተሞች መካከል በምትገኘው ደገም ባለፈው ኣርብ ሃምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ታታ በተባለ በአንድ የህዝብ ማመላለሻ ተጓዦች ላይ በታጠቁ አካላት በተፈጸመ እገታ የሰው ህይወት ስጠፋ በርካቶችም ታግተው ተወስደዋል፡፡

እገታው የተፈጸመበት ሁኔታ

እንደ የዶይቼ ቬለ የመረጃ ምንጭ አስተያየት በእለቱ ከአዲስ አበባ ወደ 130 ኪ.ሜ. ርቀት ግድም ላይ ከምትገኘው ደገም ከተማ ትንሽ ወጣ ብሎ ባለው ስፍራ ታጣቂዎች ተሽከርካሪውን በመሰባበር ተጓዦችን ሁሉ በማውረድ ከተሳፋሪዎች ጋር ስጓዙ የነበሩ አንድ የአከባቢው ተወላጅ የትራፊክ ፖሊስ እና ሾፌሩን ወዲያ ገድለው በርካቶችን ግን አፍነው ወስደውአቸዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሴ በኢትዮጵያ ስለታገቱት ተማሪዎች መግለጫ

እንደ አስተያየት ሰጪው አጋቾች በርካታ ተሳፋሪዎቹን አኖቀሬ በሚባል የቀጠር ቀበሌ በኩል ስወስዷቸው የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ከኋላ ስደርሱ ታጣቂዎች ባለመረጋጋታቸው በግምት ከ7-10 የሚሆኑ ተሳፋሪዎች በአከባቢው ባሉ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ገብተው ከእገታው አምልጠዋል፡፡ እገታው ከደገም ከተማ እጅግ ቅርብ ርቀት ላይ መፈጸሙን ያነሱት አስተያየት ሰጪው እግራቸውን ሪሂ ስታመሙ የነበረው የትራፊክ ፖሊስ እና ሾፌር ቶሎ ቶሎ መጓዝ ባለመቻላቸው በታጣቂዎች መገደላቸውንም ገልጸዋል፡፡ የጸጥታ ሃይል በቶሎ አከባቢው ላይ መድረሱ ለተወሰኑ ሰዎች ማምለጥ ምክንያት መሆኑንም በመግለጽ፤ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ያሉት ተጓዦች ግን ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል ነው ያሉት፡፡

ስለእገታው የክልሉ መንግስት ምላሽ

ተደጋጋሚ የእገታ ተግባራት በሚሰሙበት በዚህ የአዲስ አበባ-ጎጃም መንገድ ላይ ተፈጽሟል የተባለው እገታ እውነት መሆኑን ለዶይቼ ቬለ ያረጋገጡት የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ እገታውን የሚፈጽመውም በክልሉ ሸኔ ያሉት በትጥቅ መንግስትን የሚወጋው ታጣቂ ቡድን መሆኑን አስረድተዋል፡፡ “እገታውን አሸባሪው ሸነ ፈጽሞታል” ያሉት ኃላፊው ባለፉት ሳምንታት በመስመሩ ላይ በመንገደኞች ላይ ታጣቂው “የጸጥታ አካላት ስምሪትን እያየ” እገታውን ፈጽማል ሲሉም ከሰዋል፡፡

የማስለቀቂያ ገንዘብ ህይወቱን ያልታደገው ታጋች - በከሚሴ

ስለ የባለፈው ዓርብ የእገታ ተግባርም በማስመልከት አስተያየታቸው የሰጡት አቶ ኃይሉ፤ “ባለፈው ሳምንትም ደገም አከባቢ ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም የሚሁድ አንድ አውቶብስ ላይ እገታ ተፈጽሞ ከ44 የአውቶብሱ ተሳፋሪዎች ሾፌር፣ ረዳት እና አንድ በተሸከርካሪው ስጓዙ የነበሩ የትራፊክ ፖሊስ ወዲያውኑ ተገድለዋል” ነው ያሉት፡፡ ሌሎች ተሳፋሪዎችን ግን ታጣቂ ቡድኑ አፍኖ ለመሄድ ሙከራ ሲያደርግ በአቅራቢያው የነበሩ የመንግስት የጸጥታ አካላት ደርሶ የማስለቀቅ ስራ ሰርቷልም ነው ያሉት፡፡ ከተሳፋሪዎቹ አስሩ ብቻ በታጣቂዎቹ ታግተው ስወሰዱ ወደ 32 ሰዎች ግድም ወዲያውኑ መለቀቃቸውንም ገልጸዋል፡፡

ታጋቾችን የማስለቀቅ ውጥን

ተለቀዋል የተባሉት ተሳፋሪዎች የተለቀቁበትን አኳሃን በተመለከተም አቶ ኃይሉ ይህን ብለዋል፡፡ “አግቶ ስሄድ ሁሉም እኩል ስለማይሄድለት የጸጥታ አካላት ስደርሱ በእነሱ ሩጫ እኩል የሚሄዱለትን ብቻ ይዘው ይሄዳሉ እንጂ ሌላው የጸጥታ አካላት ይደርሱበታል” ብለዋል፡፡

የኦሮምያ ግጭት፤ «ሰላማዊ ሰው ይገደላል ፤ጫናው ከፍተኛ ስለሆነ የሚናገር ሰው የለም»

የታገቱትን ዜጎች የማስለቀቅ ስራም እየተሰራ ይገኛል ያሉት ሃላፊው የጸጥታ አካላት የአሰሳ ስራዎችን በየጊዜው ይከውናሉም ነው ያሉት፡፡ “ሰውሮ ይወስድበታል ተብለው በሚገመቱ አከባቢዎች ላይ የአሰሳ ስራ እየተሰራ ዜጎች ላይ አደጋ ሳይደርስ የማስለቀቅ ተግባር አለ” ብለዋል፡፡

ለችግሩ ዘለቄታዊ መፍትሄም ተጠይቀው “አደገኛ ከሆኑት ቦታዎች ውጪ በሁሉም ቦታ የጸጽታ አካላት ስምሪት ማድረግ አዳጋች” መሆኑን በማስረዳት ዜጎች ለመንግስት ጸጥታ አካላት መረጃ በመስጠት እንዲተባበሩ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በትጥቅ ውጊያ ውስጥ የሚገኙትን ወጣቶች በሰላም መመለስ ትረቶቹም መቀጠላቸውን አስረድተዋል፡፡

ስለተፈጸመው እገታ እራሱን “የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት” ካለውና መንግስት “ሸነ” እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን እስካሁን የተባለ ነገር አልተሰማም፡፡

በአሮሚያ ክልል ተደጋግሞ ስለሚፈጸመው እገታ ግን የዓለማቀፉ ማህበረሰብን ጨምሮ የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች ውትወታቸውን እያሰሙ ነው፡፡

መንግስትም በኦሮሚያ ክልል ላለፉት አምስት ዓመታት ገደማ ከሚወጋው ታጣቂ ቡድን ጋር በሰላም ችግሮችን በመፍታት የክልሉን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ወጥኖ እንደሚሰራም በተደጋጋሚ እየገለጸ ይገኛል፡፡   

    ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW