1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ለሚደርስ ጥቃት ኃላፊነቱን ማን ይውሰድ?

ሰኞ፣ ጥቅምት 3 2018

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ሐሙስ ማምሻውን በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሶዶ ዳጪ ወረዳ አከባቢ የሚንቀሳቀሱ የተባሉ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ውስጥ በደፈጣ በመግባት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሕይወት እና የንብረት ጉዳት አድርሰዋል።

Äthiopien Southwest Shoa 2025 | Bewohner erheben Vorwürfe gegen OLA
ምስል፦ Seyoum Getu/DW

በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ላይ ለቀረበው ክስ የአዛዡ አማካሪ ምላሽ

This browser does not support the audio element.

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለሚፈጸሙ የሰላማዊ ዜጎች ጥቃት  ኃላፊነቱን ማን ይውሰድ?

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ሐሙስ ማምሻውን በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሶዶ ዳጪ ወረዳ አከባቢ የሚንቀሳቀሱ የተባሉ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ውስጥ አድፍጠው በመግባት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሕይወት እና የንብረት ጉዳት አድርሰዋል።  ተጎጂዎቹ በጥቃት አድራሽነት የከሰሱት በአካባቢው የሚንቀሳቀስ  “ኦነግ-ሸኔ” ያሉት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ነው፡፡ “ ታጣቂዎቹ ከቀኑ 12 ሰዓት ገብተው 4 ሰው በመግደል 10 ሰው አግተው 15 ቤቶችን አቃጥለዋል” ያሉት አስተያየት ሰጪ የአከባቢው ነዋሪ ማኅበረሰቡ በዚህ ተደጋጋሚ ጥቃት መሰላቸቱን አመልክተዋል፡፡

 

በዚህ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አከባቢ በተደጋጋሚ ከተዘገበው የንጹሃን ዜጎች በተጨማሪ፤ በተመሳሳይ እለት ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ጊርሚጎባ ቀበሌ በደረሰ ተመሳሳይ የሰላማዊ ዜጎች ጥቃት አራት ሰዎች ተገድለው ስድስቶቹ በታጣቂዎች ስታገቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተባሉ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ “ከ11-12 ሰዓት አከባቢ ላይ ነው ኦነግ ሸኔ ባደረሰው ጥቃት ሰው በተኛበት የተጎዳብን” የሚሉት ተጎጂው የአከባቢ ነዋሪ መሰል ጥቃት ተደጋግሞ እንደሚከሰትም አንስተዋል፡፡

ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ጊርሚጎባ ቀበሌ በደረሰ ተመሳሳይ የሰላማዊ ዜጎች ጥቃት አራት ሰዎች ተገድለው ስድስቶቹ በታጣቂዎች ስታገቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተባሉ ቤቶች ተቃጥለዋል፡ምስል፦ Seyoum Getu/DW

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ስለሚቀርብበት ክስ..

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ስለሰሜን ሸዋ ዞን ወራጃርሶ ወረዳ ጊርሚጎባ ቀበሌው ጥቃት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በተደጋጋሚ በሚቀርብበት መሰል ክሶች ላይ ማስተባበያ ሰጥቷል፡፡ የኦነግ-ኦነሰ ከፍተኛ አዛዥ አማካሪ አቶ ጅሬኛ ጉደታ፤ “ንጹሐንን የመከላከል እንጂ የማጥቃት እርምጃ አይወሰድም” በማለት በሰሜን ሸዋ ዞን ጃርሶ ወረዳ በተጠቀሰው ቀበሌ ስለደረሰው ጥቃት ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ማብራሪያ “በጊሪሚጎባ ውስጥ የሚኖሩ ሆነው ወደ ኦሮሚያ ክልል መልየጡ ጫዋ፣ ሀሮ-ጨለንቆ፣ ጨዋ-ጉራሳ እና ወረጎልጃ እየተስፋፉ እቤት የሚያቃጥሉና ሀብት የሚዘርፉ” ያሏቸው ላይ ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ ስባል ሰራዊታቸው እርምጃ እንደሚወስድ ነው ያስታወቁት፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እጁ ንጹሕ ነውን?

በሰሜን ሸዋ ዞን የወረጃርሶ ወረዳ ተጎጂዎቹ ባለፈው ኃሙስ ጥቃቱበኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ስወሰድ የጥቃቱ ሰለባዎቹ በዋናነት የአከባቢው ንጹሐን ዜጎች እንደሆኑ ያስገነዝባሉ፡፡ የአከባቢው ባለሥልጣናትም ይህንኑን አረጋግጠዋል፡፡ አቶ ጅሬኛን መሰል የሰላማዊ ማህበረሰቡን አስተያየት እንዴት እንደምመለከቱ ጠየቅናቸው፡፡ እሳቸው ግን “እንግዲህ በደረሰን መረጃ ንጹሐን ዜጎች ላይ እርምጃ የሚወስድ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የለም” በማለት ይልቁንም ሰራዊታቸው ንጹሃንን ከግድያ እና ዘረፋ ለመከላከል እንደሚሰራ ሞግተዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ሓሙስ ማምሻውን በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሶዶ ዳጪ ወረዳ አከባቢ የሚንቀሳቀሱ የተባሉ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ውስጥ አድፍጠው በመግባት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የህይወት እና የንብረት ጉዳት አድርሰዋል።ምስል፦ Seyoum Getu/DW

ኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የአዲስ አበባ ጎጃም አውራ ጎዳናን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች በሚወሰዱ የእገታ እና ግድያ ድርጊቶች የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችን ጨምሮ ተጎጂዎች በተደጋጋሚ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን በተደጋጋሚ ተጠያቂ ማሰድረጋቸው አይዘነጋም፡፡ አቶ ጅሬኛ ግን፤ “በጃል መሮ ስር የሚንቀሳቀስ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በዚህ ድርጊት አይሳተፍም” ብለው በመከራከር ሰራዊታቸው “የወረደ” ያሉት መሰል ተግባራት ላይ በመሳተፍ ገንዘብ የሚጠይቅ አይደለም ብለዋል፡ ሆኖም “በኦነሰ ስም የሚዘረፍ አሉ” ያሉት አቶ ጅሬኛ መሰል ተግባራት “ህዝብን ነጻ አወጣለሁ ከሚል ሰራዊት የማይጠበቅ” ብለውታል፡፡ መሰል የሰዎች መብት ጥሰት ላይ የተሰማሩ ግን መኖራቸውን በመግለጽ፤ “እነዚህ ማጅራት መቺ እንጂ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መገለጫ የላቸውም” ነው ያሉት፡፡

በኦነሰ ላይ የሚቀርበው የሰብዓዊ ድርጅቶች ክስ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡ የሰዎችን የመዘዋወር መብት አደጋ ላይ ወድቋል” ሲል ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ባወጣው ዘለግ ባለው ሪፖርት በዚህ ሰብዓዊ ምብቶች ጥሰት ላይ ከሚሳተፉት ታጣቂዎች መካከል የኦነሰ ሰራዊት ጥቃት መኖሩን አስታውቋል፡፡ ዜጎች ላይ በሚደርሰው ግድያ፣ እገታ፣ የንብረት ዘረፋና እና ውድመት ላይ በትጥቅ ፊልሚያ ውስጥ ያሉ የኦነሰ፣ ፋኖ እና መንግስት ታጣቂዎች እንደሚሳተፉም በመግለጽ፤ የተሟላ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነትን እንዲረጋገጥም አሳስቧል፡፡

አቶ ጅሬኛ ጉዲታ ግን ይህ ዓላማችን አይደለም ይላሉ፤ “ዓላማችን አንድና አንድ የኦሮሞን ህዝብ ነጻ ማውጣት ብቻ ነው” በማለትም ውንጀላዎቹን አጥጥለዋል፡፡

እልባት አልባ ሆኖ የቀጠለ በመሰለው ግጭት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በወታደራዊ እጀባ ዜጎችን ለማጓጓዝ እንደሚሰራ ከሰሞኑ መገለጹም ይታወሳል፡፡

ሥዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ 
ታምራት ዲንሳ
 

 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW