በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የኢድ አልፈጥር በዓል ተከብሮ ዋለ
ዓርብ፣ መጋቢት 11 2018
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የኢድ አልፈጥር በዓል ተከብሮ ዋለ
ግጭት ባለባቸው አከባቢዎች በዓሉ ድባብ ቀዝቀዝ ሲል መረጋጋት በሚስተዋልባቸው የክልሉ አከባቢዎች ደግሞ እንደወትሮ በዓሉ በደማቅ ስነስርዓት ማለፉን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ያለፉትን ጢቂት ዓመታት አከባቢው ላይ በተፈጠረው ግጭት አለመረጋጋት ውስጥ ሆነው ህይወት ከሚፉ ዜጎች መሆናቸውን ገልጸው አስተያየታቸውን የሰጡን እስማኤል ሀሰን የተባሉ ነዋሪ ዛሬ በመላው ዓለም ብሎም በኢትዮጵያሙስሊሞች ተከብሮ የዋለውን የኢድ-አልፈጥር በዓልን እንደ ፈጣሪ ፍቃድ አክብረው መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡ “በዓሉ ምንም አይል፤ ኢድን አፍጥረናል ዛሬ፤ እያከበርን እንገኛለን፤ እንደ ወለጋ አከባቢ እንደ ጎጥ እንጂ እንደቀበለ እንኳ ተሰብስበን ግን አይደለም እያከበርን ያለነው” ብለዋል፡፡ በጸጥታው ስጋት እንደ ወትሮ ተሰባስበው በዓሉንማክበር በተቀዛቀዘበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ኢድን እያሳለፉ መሆኑንም በአስተያየታቸው ገልጸዋል፡፡
እንደ እስማኤል አስተያየት ከዚህ በፊት አከባቢው ፍጹም መረጋጋት ውስጥ በነበረበት ጊዜ የሚከወነው የበዓሉ አከባበር አሁን ላይ ተቀዛቅዟልም፡፡ “እኛ እንደ ወለጋ ከዚህ በፊት በዓሉን እንደው የሁለት የሶስት ቀበሌ ማህበረሰብ ሆነን ነበር አንድ ላይ ተሰባስበን በኣሉን የምናከብረው፡፡ አሁን ግን የአንድ ቀበሌ ማህበረሰብ እንኳ አንድ ላይ ተሰባስበህ በዓሉን ለማሳለፍ ስጋት አለ” በማለት ትናንት እንደለመዱት ባይሆንም እንደ ጊዜው ሁኔታ በዓሉን ማክበራቸውን አስረድተዋል፡፡
ላለፉት አምስት አመታት ግድም ግጭት ፈጽሞ ባልራቀው በዚህ አከባቢ ከአሁናዊ የፀጥታ ሁኔታው በተጨማሪ በጊዜ ሂደት በግጭት የተቀዛቀዘው የማህበረሰቡ የኢኮኖሚው ምንጭ መዳከም በዓሉ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡ “ኢኮኖሚው አሁን ከአቅም በላይ ሆኗል፡፡ በግጭት በተዳከመው የገቢ ምንጭ ላይ እየናረ የመጣው የኑሮ ሁኔታ ሌላው ራስ ምታት ነው የሆነብን፡፡ አሁን የማህበረሰቡ ትልቁ ፈተና ህይወትን ማቆየት ነውና ቆሉም ብሆን ተካፍለን በዓሉን አስታውሰን ውለናልም” ብለዋል፡፡
ከምዕራብ አርሲ ዞን ሲራሮ ወረዳ አስተያየታቸውን የሰጡ አሊዪ ዋቆ ደግሞየዘንድሮን ኢድእንደወትሮ ሁሉ በደማቅ ሀይማኖታቸውና የአብሮነት እሴት ነው የተከበረው፡፡ “በዓሉ መልካም ነበር፤ ደመቅ ባለ ሁኔታ ነው ተከበረው፡፡ እንደምናውቀው በኛ በሙስሊሞች ዘንድ ይህ በዓል ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው እንደመሆኑ በተለየ ስሜት ውስጥ ሆነን ነው የምናከብረው፡፡ በዚህ በዓል ድሆች ይታወሳሉ፤ በበዓሉ አከባበር መሃል ይረዳሉ፡፡ አንድ ወር ሙሉ ጾም ላይ ቆይተን በእርድ ያለንን አንድ ላይ በማምጣት በአብሮነትም በተለየ ስሜት የምናከብረው ነው፡፡ ኢድ የመሰባሰብም በዓል ስለሆነ የቻለ ከሩቅ ጭምር ይመጣል፤ ካልሆነለት ግን የቅርቦቹ ጎረበት አይል ዘመድ አንድ ላይ ነው ተሰባስበን እያሳለፍን ያለነው” ሲሉ የበዓሉ ደማቅ ድባብ አስረድተዋል፡፡
በጅማም የኢድ በዓል በደማቅ ሁኔታ ነው ተከብሮ የዋለው፡፡ ማልደው ለሶላትተሰባስበው ከሰዓቱን ደግሞ በአንድነት በኣሉን ከቤተሰብና ወዳጆቻቸው ጋር እያሳለፉ የሚገኙት ሙስጠፋ አባገሮ ስለዘንድሮ ኢድ አከባበር አስተያየታቸውን ካጋሩን ናቸው፡፡ “ከጎረቤት ጋር በዓሉ በጥሩ ሁኔታ እያለፈ ነው” ሲሉ ኢድ በአብሮነት እየተከበረ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ጸሀይ ጫኔ