1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ትምህርት

በኦሮሚያ ዳግም ትምህርት የማስጀመር ጥሪ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 5 2013

በኦሮሚያ ክልል ከፊታችን ሰኞ ህዳር 07 ቀን» 2013 ዓ.ም ጀምሮ በመላው የክልሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንደሚጀመር ተገለጠ። የክልሉ የትምህርት ቢሮ ለኮቪድ መከላከል እና መምህራንን ማሰልጠን ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቀዋል። 

Äthiopien Dr. Tola Beriso
ምስል፦ S. Getu/DW

ከሰኞ ኅዳር 07 ቀን፣ 2013 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል

This browser does not support the audio element.

በኦሮሚያ ክልል ከሰኞ ኅዳር 07 ቀን» 2013 ዓ.ም ጀምሮ በመላው የክልሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንደሚጀመር ተገለጠ። የክልሉ የትምህርት ቢሮ ለኮቪድ መከላከል እና መምህራንን ማሰልጠን ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቀዋል። 

የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክትር ቶላ በሪሶ ዛሬ መገናኛ ለብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ከዚህ በላይ ትማሪዎችን ከትምህርት ቤት ማራቅ አግባብ ባለመሆኑ የፀጥታ ዝግጅት ተደርጎና የኮሮና ተዋሲ ስርጭትን በሚገታ አኳኋን ትምህርት ለመጀመር ዝግጅት ተጠናቋል በቭለዋል፡፡

ከጥቅምት 18 ጀምሮ ነባር የ8ኛ እና12 ክፍል ተማሪዎች በማካካሻ ትምህርት ላይ መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው ከ30 ቀናት በኋላ እነሱ የሚኒስትሪ እና የመሰናዶ ፈተናቸውን ሲያጠናቂቁ አዳዲስ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንደሚመለሱ ገልጸዋል፡፡

ከዚያ ውጭ ግን በሁሉም ደረጃ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ከሰኞ ጀምሮ ወደ መማር ማስተማር ገበታው ይመለሳሉ ብለዋል፡፡ በተያዘው ዓመት በኦሮሚያ ክልል 11.2 ሚሊየን ተማሪዎችን ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት ቢደረግም እስካሁን ወደ ትምህርት ቤት በመምጣት የተመዘገቡት 9.8 ሚሊዮን ያህል ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW