በኦሮሞ ማሕበረሰብ ዞን ዉጊያ ቀጥሏል
ረቡዕ፣ ኅዳር 1 2014![Äthiopien Stadtbild aus der Stadt Kemise in der Amhara-Region](https://static.dw.com/image/59781804_800.webp)
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር፣ መንግሥትን የሚደግፉ ሚሊሺያዎችና የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ታጣቂዎች በአማራ ክልል በኦሮሞ ማህበረሰብ ልዩ ዞን ዉጊያ መግጠማቸዉን የዞኑ ባለሥልጣናትና ነዋሪዎች አስታወቁ። የሕወሓትና የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ጦር (ኦነጦ) የኦሮሞ ልዩ ዞን ዋና ከተማ ከሚሴን ባለፈዉ ሳምንት ተቆጣጥረዋታል። የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አሕመድ ሐሳን እንደሚሉት ግን ከሚሴ፣ ጨፋ ሮቢት፣ ጃራና በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረገዉ ዉጊያ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ