በከማሺ ዞን የትምህርት ቤቶች ይዞታ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2011ማስታወቂያ
ሁለት ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመው እንደ ነበር የካማሺ ዞን አስተዳደር የሆኑት አቶ ታርኩ ኩመራ ለዶይቼ ቬለ DW ተናግረዋል። ከ20ሺ በላይ አንደኛ ደረጃ ተማርዎች ደግሞ በትምህርት ገበታቸው ላይ አልነበሩም። ከመስከረም 2011 ዓ.ም መጀመሪያ አንስቶ በካመሺ ዞን ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ከአምሳ ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል፣ በርካቶች ለሞት ተዳርጓል፣ በሚሊዩን የሚቆጠር ንብረት ደግሞ ባክኗል። ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ባንክ፣ ጤና ጣቢያዎችና ትምህርት ተቋማትም አገልግሎት መስጠት ከማቆም አልፎ የፈራረሱና የወደሙም መኖራቸውን የካማሺ ዞን ዋና አስተዳደር የሆኑት አቶ ታሪኩ ኩመራ ገልጸዋል። ለብዙ ወራት በነበረው አለመረጋጋት በካማሺ ዞንና በስሩ በሚገኙ አጋሎሜጥ እና ቦሎ ጅጋንፎይ በተባሉ ወረዳዎች ዘጠኝ የሚደርሱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱንና ከነዚህም ሁለት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶት ደግሞ ሙሉ በመሉ ወድመው እንደ ነበር ነው የዞኑ አስተዳዳር አቶ ታሪኩ የገለጹት። የአሶሳው ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ