1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 15 2017

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ 15 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በወረዳው ጫቢ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በአንድ ሳምንት ልዩነት ሁለት ጊዜ በታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን አስተያየታቸውን ለዲዳቢሊው የሰጡ ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡

Infografik GRAPHIC Karte Amuru Woreda, Äthiopien
ምስል፦ DW

ምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ

This browser does not support the audio element.

በኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ 15 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በወረዳው ጫቢ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በአንድ ሳምንት ልዩነት ሁለት ጊዜ በታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን አስተያየታቸውን ለዲዳቢሊው የሰጡ ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ፈቃዱ ጥቃቱ መድረሱን አረጋግጠው በአካባቢ ይንቀሳቀሳሉ ያሏአቸው እና ጽንፈኛ ቡድን ብለው የጠሩአቸው ሐይሎች ጥቃቱን ማድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

የታጣቂዎች እንቅስቃሴ በስፋት በሚስተዋልበት የምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ በትናንትናው ዕለት በወረዳዋ ጨቢ በሚባል ቦታ በደረሰው ጥቃት የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ የሠላማዊ ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ በተደራጅ መልኩ ደርሷል የተባለው ጥቃት በከባድ መሳሪያ የታገዘ እንደሆነ አስተያየታቸውን የሠጡን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ አመልክተዋል፡፡ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስባት ኪረሙ ወረዳ ከዚህ ቀደም በ2014 ዓ.ም በተከሰተው የጸጥታ ችግር በወረዳው ስር ከሚገኙ 18 ቀበሌዎች ሰዎች ተፈናቅለው እንደነበር ተገልጿል፡፡

በአሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ

‹‹ ጠዋት ላይ በከባድ መሳሪያ እንደ ዲሽቃና ብሬን ታጥቀው ውጊያ ጀምሮ በአርሶ አድሮችን ጨምሮ 15 ሰዎች ናቸው ህይወታቸው ያለፈው፡፡ ሌሎች በመኖርያ ቤታቸው ነው የተገደሉት፣ሌሎች ደግሞ እርሻ ማሳ አካባቢ ነው ህይታቸው ያለፈው፡፡ ህይወታው ካለፈው መካከል 9 በጥይቶ የጠመቱ ሲሆን 6ቱ ደግሞ በስለታ መሳሪያ ነው የተመቱት፡፡ ጥቃቱን ካደረሱ በኀላ ከብት፣በግና ሌሎችም የቁም እንስሳት ዘርፎ ነው የሔዱት፡፡››

የታጣቂዎችን ጥቃት ሸሽተው ከሀሙሩ ወረዳ የተፈናቀሉ ሰዎችምስል፦ Alemenew Mekonnen/DW

ሌላው ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪም ጨቢ በሚባል ቦታ በትናንትናው ዕለት በደረሰው ጥቃት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቋል፡፡ጨቢ/በደሳ ተብሎ በሚታወቅ ቦታ ባለፈው ሳምንት አርብ በተመሳሳይ ታጣቂዎቹ አድርሷል በተባለው ጥቃት አንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነዋሪው አብራርተዋል፡፡

‹‹በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው 12 ሰዎች ነበሩ፡፡ በኀላ ላይ በጥቃቱ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ 3 ሰዎችም መትረፍ አልቻሉም፡፡ ከባ መሳሪያ ነው ሲተኮስ የነበረው፡፡ በጥቃ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፖሊስ መኪና ነው ወደ ከተማ የመጡት፡፡››

በኦሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ ልጆቻቸው ወደ ታጣቂዎች ተቀላቀሉ የተባሉ 17 ሰዎች ታሰሩ

በኪረሙ ወረዳ በ2014 ዓ.ም በተከሰተው ግጭት 50ሺ የሚሆኑ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው መቆየታቸውን የወረዳው አስተዳደሪ አቶ ብርሀኑ ፈቃዱ አመልክተዋል፡፡  አስተዳዳሪው  ከወረዳው 18 ከሚደርሱ ቀበሌዎች ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ወደቤታቸው ተመልሰው በወረዳው አንጻራዊ ሰላም ሰፍኖ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ትናንት በወረዳው ጽንፈኛ ቡድን ያሏቸው ሀይሎች ባደረሱት ጥቃት የሰው ህይወት ማለፉን አረጋግጠዋል፡፡

‹‹ ትናንት ጠዋት 1፡30 ገደማ ጨቢ/በደሳ የሚባል ቦታ በሰላማዊ ሰዎች እና ሚሊሻ አባላት ላይ ታጣቂዎቹ ተኩስ ከፍተው የ12 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ሶስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ እነዚህ ሐይሎች በተደጋጋሚ ጥቃት እና ዘረፍ የሚፈጽሙ ሐይሎች ናቸው፡፡››

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ እና በሆሮ ጉዱሮ ወለጋ ዞን ጃርዳጋ ጀርና አቤዶንሮ በሚባሉ ወረዳዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃች የደረሱ ሲሆን የበርካታ ሰዎች ህይወት እያለፈ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW