1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኪሲዋህሊ ነጻነት ሆነ

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2016

የቻጋ ሕዝብ በአፍሪቃ እጅግ ታዋቂ እና ትልቁ በሆነው የኪሊማንጃሮ ተራራ ተዳፋታማ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ናቸው ። ህዝቡ የተራራውን አናት ኪቦ ብለው ይጠሩታል። ነገር ግን በዘመናዊው ታሪክ ታንዛንያውያን ተማሪዎች የኪሊማንጃሮ ተራራ በጀርመን ሚሺነሪ ዮሃንስ ሬብማን አማካኝነት በ1848 እንደተገኘ ያስባሉ ።

Teaser Shadows of german colonialism AMH
ምስል DW

የኪሊማንጃሮ ተራራ ጉዳይ

የቻጋ ሕዝብ በአፍሪቃ እጅግ ታዋቂ እና ትልቁ በሆነው የኪሊማንጃሮ ተራራ ተዳፋታማ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ናቸው ። ህዝቡ የተራራውን አናት ኪቦ ብለው ይጠሩታል።

ነገር ግን በዘመናዊው ታሪክ ታንዛንያውያን ተማሪዎች የኪሊማንጃሮ ተራራ  በጀርመን ሚሺነሪ ዮሃንስ ሬብማን  አማካኝነት በ1848 እንደተገኘ ያስባሉ ። ነገር ግን የጀርመናዊ የመልክዓ ምድር ተመራማሪ ሃንስ ሜየር በ1889 የተራራው ጫአናት ላይ በደረሰ ጊዜ ስያሜውን ከኪቦ ወደ ካይሰር ቪልሄልም ቀየረው ።  

የኪሊማንጃሮ ተራራ ለአካባቢው የቻጋ ምህበረሰብ የነበረው ባህላዊ ጠቀሜታ ሙሉ በሙሉ ችላ ተብሏል። ነገር ግን አውሮጳውያኑ አሳሾች በማህበረሰቡ ዘንድ እንደምልክት የሚታዩ ልዩ አካባቢዎችን እንደገና መሰየም የሚያመጣላቸውን ጠቀሜታ ጠንቅቀው ያውቃሉ ። በዚህም ራሳቸውን አዲሶቹ የአፍሪቃ ጌቶች እና ነባር አፍሪቃውያን ነዋሪዎችን ለማሰልጠን እንደመጡም ራሳቸውን ያቀርባሉ ። ከዚህ የተነሳ በአካባቢው ነዋሪዎች ይጠሩ የነበሩ መሰል አካባቢዎች ስሞች እንዳይጠሩ ብሎም በሂደት እንዲረሱ  አድርጓቸዋል።

 

በጎርጎርሳውያኑ 1964 የተባበረችው ታንዛኒያን መወለድ እና የኪሊማንጃሮ ካይሰር ቪልሄልም ጫፍ የኡሁሩ ጫፍ ወይም «በኪስዋሂሊ ነጻነት ሆነ» የሚለውን ስያሜ በማግኘቱ ተዘክሯል።

 

በምስራቅ አፍሪቃ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘው ታላቁ የቪክቶሪያ ሐይቅ ዛሬም ድረስ በ19ኛ ክፍለ ዘመን በነበረች የብሪታንያ ንግስት እንደተሰየመ ይገኛል። የጀርመን ሰፋሪ ብቸኛ ቅኝ ግዛት የነበረችው ናሚቢያም እንዲሁ እስከዛሬም ድረስ በበርካታ የጀርመን ስሞች ተሞልታለች።

በወቅቱ የጀርመን የመልክዓምድር አጥኚዎች ከነበሩት  እንደ ፍሬድሪክ ራትዝል ያሉ ሰዎች ጀርመን እንደ አንድ ‘ኃያል ሀገር' ደካማ ወደሚባሉት አገሮች የመስፋፋት መብት እንዳላት ምክረሃሳብ በማቅረብ በቅኝ አገዛዝ አስተሳሰብ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ችለዋል።

የ"Lebensraum" ወይም የህያው ህዋ ርዕዮተ አለም ለጀርመን ቅኝ ግዛት ማፅደቂያነት ያገለግል ነበር። በቅኝ የተያዙ መሬቶችንም  ለጀርመን ባህል ምቹ ማድረግ ነበረባቸው። "Lebensraum" በኋላ ላይ የናዚ አስተሳሰብ ዋና አራማጅ  ሆነ።

በቅኝ ገዥዎች አፈና እና ሁከት የአንድ ህዝብ ህልውና ከተናጋ በኋላም ቢሆን የህዝቡን ማንነት መንጠቅ ደግሞ የበለጠ ህዝቡን መቆጣጠራቸውን ለማረጋገጥ ወሳኝ ምክንያት ሆኖላቸው ነበር።

ቅኝ ገዢዎች እንዴት ይታወሳሉ

ነገር ግን የቅኝ ግዛት ጊዜን  ማስታወስ ፈታኝ ነው፤ ፊውዳል ጀርመኖች ለሄርማን ቮን ዊስማን በ1900 መጀመሪያ አካባቢ ደፋር፣ ጀብደኛ እና ታላቅ አፍሪቃዊ ብለው ቅጽል ስም አውጥተውለት ነበር። እርሱም ግዛቱን የያዘበት መንገድ ግዛቱን የያዘበት መንገd eየተለየ እንዲሆን አድርጎታል። እ.ኤ.አ. በ1905 በዳሬሰላም  ሃውልት ተተከለት ። በተጨማሪም በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን እና በሌሎችም ስፍራዎች ለእርሱ ክብር ሲባል ጎዳናዎች ተሰይመዋል።

ነገር ግን ለምስራቅ አፍሪቃውያን ቪስማን የለየለት ጨካኝ ነበር ። ወታደሮቹም በየአካባቢው በግድያ ፣ አስገድዶ መድፈር እና የጉዞ ቅጣት በመጣል ጭምር በአጠቃላይ ህዝቡን በማሸበር ስራ ላይ የተጠመዱ ነበሩ ።

የቪስማን ሐውልት በክፍለዘመኑ አጋማሽ ላይ ሐምቡርግ ውስጥ በድጋሚ ሳይቆም በፊት በብሪታንያ ቅኝ ገዢዎች ተወግዶ ነበር። በኋላ ግን ያንኑ የጀርመናዊውን ፊውዳል  ክብርን በመቃወም አዲሱ የጀርመን ትውልድ ተማሪዎች ሀውልቱን በ1967 አፈረሱት ።

የጀርመን ሙዚየሞች የበርካታ አፍሪቃውያንን አጽም እንዴት ሊያሰባስብ ቻለ?

ምናልባት ታንዛንያውያን ጀርመኖችን ከሚሟገቱባቸው የጋር የቅኝ ግዛት ታሪኮቻቸው ውስጥ  በተለይ ከታንዛንያ ተሰርቀው እንደ የጦር ምርኮ ወደ ጀርመን የተወሰዱ የዕደ ጥበብ ውጤቶች እና የሰው ልጅ አጽሞች  በዋነናነት ተጠቃሾች ናቸው ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የአፍሪካ የራስ ቅሎች ከቅኝ ግዛት ጦር ሜዳዎች አልያም  ከመቃብር ተሰርቀው የዘረኝነት ጥናት እና ምርምር ሊከናወንባቸው አልያም ሙዝየም ውስጥ ለእይታ እንዲቀርቡ ወደ ጀርመን ተወስደዋል ። ከእነዚህ  አስከሬኖች መካከል በጣም ጥቂቶቹ ብቻናቸው በሀገር ባህል መሰረት በክብር እንዲቀበሩ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱት ።

 የታንዛኒያ የታሪክ ተመራማሪዎች እና በአስከፊው የቅኝ ግዛት ወቅት የተገደሉ ሰዎች የልጅ ልጆች የአያቶቻቸው አጽም እንዲመለስላቸው ለረዥም ጊዜ ሲጠይቁ ቆይተዋል። ታንዛንያው ውስጥ የተፈጸመው አስከፊ የቅኝ አገዛዝ ያደረሰውን ጥፋት የመዘገቡ ጥቂት የታሪክ ድርሳናት ቢኖሩም ማህበረሰቡ በአፈ ታሪክ እየተቀባበለ ለትውልድ ያስተላለፈው ግን ልቆ ይታያል ። 

በጎርጎርሳውያኑ ህዳር  2023 የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ሶንግያን በጎበኙበት ወቅት ጀርመን በማጂ ማጂ ጦርነት ለፈጸመችው ግፍ ታንዛንያውያንን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጀርመን የሰዎቹን አጽም ወደ የልጅ ልጆቻቸው  ምድር ለመመለስ እየሰራች ነው ብለዋል።

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW