1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ 18 ሰዎች ተገደሉ፤ ሶስት ታገቱ

ነጋሣ ደሳለኝ
ዓርብ፣ ግንቦት 15 2017

በተጨማሪ 10 ሰዎች ወደ ነቀምት ሆስፒታል ለህክምና መሄዳቸውን አስተያየጣውን የሰጡን ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ በወረዳው ከተማ ሶጌ ከተባለው ከተማ በ45 ኪ.ሜ ርቀት ገደማ ላይ በሚትገኘው አንገር መጢ ወይም ‹‹አይሻንጅድም›› በተባለው ከተማ ጥቃቱ መድረሱን የተናገሩት አንድ የአካባቢው ነዋሪ የተገደሉት ሁሉም ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸው አመልክተዋል፡፡

የሰሞኑ ጥቃት የደረሰዉ በካማሺ ዞን ምዥንጋ ወረዳ ዋና ከተማ ከሆነችዉ ሶጌ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ ነዉ
በበኒ ሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን ዋና ከተማ።ካማሺ።በካማሺ ዞን ታዛቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርሱት ግድያና ጥቃት ባለፉት 2 ዓመታት ጋብ ብሎ ነበርምስል፦ Negassa Dessalegn/DW

በካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ 18 ሰዎች ተገደሉ፤ ሶስት ታገቱ

This browser does not support the audio element.

 

በበኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ምዥጋ በተባለ ወረዳውስጥ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት 18 ሰዎች ገደሉ።ሌሎች 10 አቆሰሉ፤ 3 አገቱም።የአካባቢዉ ነዋሪዎች «ድንገት ተከፈተ» ባሉት ጥቃት ከታገቱት አንዱ አንዱ ሞቶ መገኙቱን ገልጸዋል፡ታጣቂዎች መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋልም።ነዋሪዎቹ ለጥቃቱ ሸኔ ተብሎ የሚጠራዉን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አማፂ ቡድንን ተጠያቂ ያደርጋሉ። የክልሉ ፖሊስ ግን ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝ አስተውቋል፡፡የአሶሳዉ ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

በካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ለሊት 11፡00 ሰዓት ገደማ ላይ ደርሷል በተባለው ጥቃት የሰላማዊ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጸዋል፡፡ ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪ 10 ሰዎች ወደ ነቀምት ሆስፒታል ለህክምና መሄዳቸውን አስተያየጣውን የሰጡን ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ በወረዳው ከተማ ሶጌ ከተባለው ከተማ በ45 ኪ.ሜ ርቀት ገደማ ላይ በሚትገኘው አንገር መጢ ወይም ‹‹አይሻንጅድም›› በተባለው ከተማ ጥቃቱ መድረሱን የተናገሩት አንድ የአካባቢው ነዋሪ የተገደሉት ሁሉም ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸው አመልክተዋል፡፡

ጥቃቱ በድንገት መከሰቱን የተናገሩት ነዋሪው በአካባቢው የሚገኙ ጸጥታ ሐይሎች ጋር ለሰዓት የተኩስ ልውውጥ እንደነበር እና ታጣቂዎቹም ከአካባቢው መውጣቸውን ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው ከዚህ ቀደም በተደረጉ የሰላም ገባኤዎች እና በዞኑ ውስጥ ከነበሩት ታጣቂዎች ጋር  ደግሞ የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኃላ ሰላም መስፈኑን ነዋሪው አብራርተዋል፡፡

‹‹ጥቃቱ ሠላማዊ ሰዎችን እላማ ያደረገ ነው››

ሌላው በምዥጋ ወረዳ ነዋሪ የሆኑትና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈጉ ነዋሪ ጥቃቱን አስመልክቶ እንደተናገሩት በጥቃቱ ቆስሎ ከበሩት 14 ሰዎች መካከል የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን አመልክተዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸበት ቀበሌ የተለያዩ ማህበረሰብ ከፍሎች በጋራ የሚኖርበት ከተማ እንደሆነ ያነሱት ነዋሪው ጥቃቱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ብሏል፡፡

ታጣቂዎቹ ሶስት ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውንና ቤት ማቃጠላቸው የተነገረ ሲሆን  በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ሐይሎች ችግር የተፈጸረበትን ቦታ መቆጣጠራቸውን  ነዋሪው ተናግረዋል፡፡ በምዥጋ ወረዳ ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ በሚሊሻ ሀሎች  እርምጅ ተወስዶባቸው እንደ ነበር አመልክተዋል፡፡

‹‹ጉዳዩን እያጣራን ነው›› የክልሉ ፖሊስ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንበምዥጋ ወረዳ የተከሰተውን የታጣቂዎችን ጥቃት ጉዳይ እያጣራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀሩን ኡመር ስለ ጉዳዩ ዝርዝር መረጃ ከተጣራ በኃላ እንደሚገልጹ አመልክተዋል፡፡ ጥቃት አድርሰዋል ከተባሉት መንግስት ሸኔ የሚላቸው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መረጃ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልሰመረም፡፡

የበኒ ሻንጉል-ጉሙዝ ዋና ከተማ አሶሳ።የክልሉ ፖሊስ ሰሞኑን በካማሺ ዞን ሥለደረሰዉ ጥቃት መረጃ እያሰባሰበ መሆኑን አስታዉቋል።ምስል፦ Negassa Dessalegen/DW

በካማሺ ዞን ከሁለት ዓመት ወዲህ በታጣቂዎች የብዙ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ይሄ የመጀመሪያ ሲሆን በዞኑ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ታጣቂዎች ጋር የሰላም ስምምነት ከተደረሰ ወዲህ በአካባቢው  ሰላም መስፈኑን የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም ይፋ አድርጓል፡፡ ከአጎራባች ዞኖች ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች የሚከሰቱ የሰላም ችግሮች ደግሞ በተደረጉ ተደጋጋሚ የሆኑ የሰላም ጉባኤዎች ችግሩ መፈታቱን ከዚህ ቀደም ተዘግበዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW