1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በካን የፊልም ፌስቲቫል ደምቃ የታየችው ኢትዮጵያዊት

እሑድ፣ ሰኔ 3 2010

ባለፈው ግንቦት ወር በፈረንሳይ በተካሔደው የካን የፊልም ፌስቲቫል ከዝነኛ የፊልም ባለሙያዎች ጎን በቀይ ምንጣፍ ላይ የታየችው ዮርዳኖስ ሽፈራው ቀልብ ስባ ነበር። ዮርዳኖስ የተወነችበት ካፋርናም የተባለው ፊልም በፈረንሳይ አገር በሚካሔደው የካን ፊልም ፌስቲቫል ሽልማት አግኝቷል።

Film Capharnaum Yordanos Shiferaw
ምስል Getty Images/AFP/A. Poujoulat

በካን የፊል ፌስቲቫል ደምቃ የታየችው ኢትዮጵያዊት

This browser does not support the audio element.

ባለፈው ግንቦት ወር በፈረንሳይ በተካሔደው የካን የፊልም ፌስቲቫል ከዝነኛ የፊልም ባለሙያዎች ጎን በቀይ ምንጣፍ ላይ የታየችው ዮርዳኖስ ሽፈራው ቀልብ ስባ ነበር። ዮርዳኖስ በመርኃ-ግብሩ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚታወቀውን ጥበብ ቀሚስ ለብሳ ታይታለች። ዮርዳኖስ በካን የተገኘችው ካፋርናም  በተባለ ፊልም ላይ በትወና በመሳተፏ ነበር። ዮርዳኖስ ነዋሪነቷ በዮርዳኖስ ሲሆን በቤት ሰራተኝነት ትሰራለች። ዮርዳኖስ በፊልሙ የተጫወተጫት ገጸ-ባሕሪ የገጠማት ውጣ ውረድ ያለፈችበት ፈተና በእውነተኛ ሕይወቷ እንደሆነ እያለቀሰች ለጋዜጠኞች ተናግራለች። ዮርዳኖስ የተወነችበት ካፋርናም የተባለው ፊልም በፈረንሳይ አገር በሚካሔደው የካን ፊልም ፌስቲቫል ሽልማት አግኝቷል። በዛሬው መሰናዶ ሐይማኖት ጥሩነህ አነጋግራታለች።

ሐይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW