በኮሪያ ጦርነት የተዋጉ ኢትዮጵያዉያን መታሰቢያ በዋሽግተን
ማክሰኞ፣ ኅዳር 9 2018
በ1940ዎቹ ኮሪያ ልሳነ ምድር በተደረገዉ ጦርነት የተዋጉ ኢትዮጵያዉያን ወታደሮች ዋሽግተን ዲሲ-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በ,ተደረገ ሥርዓታ ላይ ታስበዋል።ዋንግሽተን ዲሲና በአካባቢዉ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉን በተ,ካፈሉበት ሥነ ሥርዓት ላይ ለኢትዮጵያዉያን አርበኞች ምሥጋና ቀርቦላቸዋል።
ሻምበል ከተማ ጆባ በካሎ በ1944ዓ:ም በኮርያ ጦርነት የሁለተኛ ቃኘው አባል ሆነው ዘምተዋል:: ሻምበል ከተማ ስለኮርያ ዘመቻ ሲያወሱ፣" የክቡር ዘበኛው ጦር በባቡር ከለገሃር ተነስተው እስከ ጅቡቲ ድረስ እንደሄዱ እና ከጅቡቲ በመርከብ ለ18 ቀናት ተጉዘው ኮርያ:ቡዛን የምትባል ከተማ እንደገቡ ይናገራሉ:: በቡዛን ወደ ሁለት ወር ገደማ የጦር ልምምድ አድርገው ኦካሃዋ ወደምትባል ከተማ ከአሜሪካን ወታደርች ጎን በመሰለፍ ተዋግተዋል:: ሻምበል ከተማ በጦር ሜዳ ውሎአቸው ግዳጃቸውን በተገቢ ሁኔታ ተወጥተዋል::በ1945 ዓ:ም ከኮሪያ ተመልሰው በክቡር ዘበኛ መደበኛ አገልግሎታቸውን በመቀጠል በሻምበልነት አገልግለዋል፡፡
በ1986 ዓ:ም ወደ አሜሪካ ካ ሀገር በመምጣት ከልጆቻቸው ጋር በካልፎርኒያ ግዛት እየኖሩ የሚገኙት ሻምበል ከተማ፣አሁን የ102 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ ሲሆኑ፣ሰሞኑን በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተካሄደው የኮሪያ ዘመቻ መታሰቢያ በዓል ላይ ዕውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆኑት የታሪክ መምህርና የማኀበራዊ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ተፈራ ኃይሉ፣የሰሞኑበክብረ በዓል፣እንደ ሻምበል ከተማ ጆባ ሁሉ በኮሪያ ዘመቻ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ምስጋና ለማቅረብ የተዘጋጀ እንደነበር ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።
''የኮሪያ ዘመቻ 75 ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ለምን የእኛን አባቶች አናከብርም ለምን አናመሰግናቸውም በሚል የተጀመረ ነው። ይህም፣አንደኛ የእነሱን የአርበኝነት መንፈስ ማክበርና ሁለተኛ ደግሞ እዛ ላደረጉት ነገር የምስጋና የማክበሪያም ነበር። ''
ኢትዮጵያ ተሳትፎ በኮሪያ ጦርነት
በኮሪያ ልሳነ ምድር ጦርነት በተቀሰቀሰበት ወቅት ፣ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቻርተሩ መስረት ጥሪ ሲያቀርብላት ጥያቄውን ተቀብላ ወታደሮቿን አዝምታለች።
የኮሪያ ዘማች ኢትዮጵያውያን፣በወቅቱ ያስመዘገቡትን አኩሪ ጀብዱ በተመለከተ የታሪኩ መምህሩ አቶ ተፈራ እንደሚከተለው አውስተዋል።
''በተለይ ኢትዮጵያኖች አገርን አቋርጠው፣በመርከብ ተጉዘው አባቶቻችን በጣም ረጅም መንገድ ተጉዞው ፣ምንም የማያውቁትን እና ሰምተውትም የማያውቁትን ሃገር ኮሪያ የሚባል ሃገር ደርሰው፣ በእዛም ደግሞ ከፍተኛ ቅዝቃዜ የበረዶ አገር የበረዶ ወቅት ያንን ተቋቁመው ትልቅ ተጋድሎ ያድርጉበት፣ እሱም ብቻ ሳይሆን በእዛ በጦርነቱ ወቅት ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር በመሰለፍ ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሌሎች አጋሮችን ያኮሩበት በተለይ ኢትዮጵያኖች የገጠሙት ከቻይና ወታደሮች ጋር ነበር እና ከፍተኛ ድልን በመቀዳጀት የደረሱበት፣ከእዛም በኋላ ከመመለሳቸው በፊት በኮሪያ ከማንኛውም ሀገሮች በላይ ባንዲራችን የተውለበለበት፣ያም የሆንበት ምክንያት አንድም የተማረከ ወታደር ባለመኖሩ፣ኢትዮጵያ በዩናይትድ ኔሽንስ በነበራትም በአሜሪካም ትልቅ ዕውቅና ያገኘች እዛም በኮሪያ ማኅበረሰብ ትልቅ ፍቅርና አክብሮት ያላቸው ሆኖ እንዲገኙ የተደረገ ነው። ''
የኮሪያ ዘማች ልጆች ማኀበር በአሜሪካ
በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የሆኑት አቶ መስፍን ተክሉ፣የኮሪያ ዘማች ልጅ ሲሆኑ፣ የኮሪያ ዘማች ልጆች እና የልጅ ልጆች ማኀበር በአሜሪካ ሰብሳቢ ናቸው።
''አባቶች የተወሰኑ ተሰባሰቡና ኮሎኔል እምዕላሉ የሚባሉ ፣እነ ኮሎኔል መለስ ማኀበር አቋቋሙ። የአባቶችን ማኀበር ካቋቋሙ በኋላ አባላቶቻቸውን መሰብሰብ ጀመሩ። ማኀበራቸውን አቋቁመው ከኮሪያ መንግስት ጋር አፍንጮ በር ላይ ትልቅ ሙዚየም ተሰርቶላቸው፣ልክ ኮሪያ ላይ እንደተሰራው ሐውልት ኢትዮጵያ ላይም ሐውልታቸው ተሰርቶ እንዲዘከሩ አድርገዋል። እና አሁን እየተመናመኑ መጡ። አሁን የሚመሩት ኮሎኔል እስጢፋኖስ ይባላሉ፣ከ90 ዓመት በላይ የሆኑ አባት ናቸው። እንግዲህ የእነርሱ ታሪክ እንዳይጠፋ ነው፣እኛ ልጆቻቸው፣መቀጠል አለበት ገና ያልተነካ ብዙ ያልተመለከታቸው ነበር። ለሰላሳ ዓመታት ብዙ አልተዘመርላቸውም፣ለምን አንሰባስብም በማለት እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ለማዘጋጀት በቃን። ''
አቶ መስፍን፣የአባታቸውንና የሌሎች ዘማችኢትዮጵያውያን አኩሪ የገድል ታሪክ ለማስቀጠል የሚያስችል እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
''ታሪካቸው ብዙ ነበር የአባቴ ማስታወሻዎችን አሉ። ልብስና ሊሻኖቹን አሁን በሙሉ በክብር አሁን እናታችን አልፋልች፣አስቀምጣልኝ ነበር እና እንግዲህ ታሪካቸው ይቀጥላል በሚል ነገር አሁን አሜሪካ አገር ውስጥ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ተነስቻለሁ። ''ብለዋል።
ታሪኩ ኃይሉ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ