በኮብል ስቶን የመንገድ ስራ የተሰማሩ ወጣቶች
ዓርብ፣ መጋቢት 6 2005ማስታወቂያ
በአንዳንድ የኢትዮጵያ ከተሞች « የኮብል እስቶን» መንገዶች ይታያሉ። በዚህ የተቀረፁ ድንጋዮችን በመደርደር የሚሰራው የመንገድ ስራ ላይ ደሳለኝ ተስፋዬ ፣ሃና ለማ እና ቢንያም ከድር ተሰማርተው ይሰራሉ። ደሳለኝ ትምህርቱን ከ10ኛ ክፍል፤ ሃና ደግሞ ከ8ኛ ነው ያቋረጡት። ቢንያም ከድር ደግሞ ሃና እና ደሳለኝን በመንገድ ስራ ቀጥሮ ያሰራል። እንዴት ለዚህ እንደበቃ ገልፆልናል።
ደሳለኝ ምንም እንኳን ጥሩ ውጤት ባይመጣለትም እስከ 10ኛ ክፍል ትምህርቱን ተከታትሏል። የኮብል እስቶን ስራ በአሁኑ ሰዓት የተማረውም ያልተማረው እየሰራው ይገኛል ይላል ወጣቱ። የወደፊት አላማው በትምህርቱ መቀጠል ነው። ሃና ደግሞ ሱቅ መክፈት ትፈልጋለች። ወጣቷ ወደዚህ የመንገድ ስራ ከመግባቷ በፊት በቤት ሰራተኝነትም ተቀጥራ ለሁለት አመት ሰርታለች። ሁለቱንም የስራ መስኮች ታነፃፅራለች።
የሁሉንም መልስ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ሒሩት መለሰ