1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኮንሶ ዞንና በአጎራባች ወረዳዎች ታጣቂዎች በርካቶችን ገደሉ

ሐሙስ፣ ኅዳር 10 2013

በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞን እና በሁለት አጎራባች ወረዳዎች ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ።  የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ እንዳሉት ጥቃቱ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት የተፈጸመው በኮንሶ ዞን ፣ በአማሮ አና በቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ነው።

Äthiopien Konflikt zwischen Konso & Ale
ምስል Ale Communication Office

በኮንሶ ዞንና በአጎራባች ወረዳዎች ታጣቂዎች በርካቶች መግደላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞን እና በሁለት አጎራባች ወረዳዎች ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ። 
የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ እንዳሉት ጥቃቱ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት የተፈጸመው በኮንሶ ዞን ፣ በአማሮ አና በቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ነው።
በአካባቢዎቹ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ለዶይቸ ቬለ ያረጋገጡት የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዴ ይሁንእንጂ በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን እየተለየ ይገኛል ብለዋል።
በአሁኑወቅት መንግስት ጥቃቱ ወደ ተፈጸመባቸው ቀበሌያት የፀጥታ አባላትን ያሰማራ ሲሆን የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ ለመያዝም ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 
እሸቴ በቀለ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW