1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወርቅ ምርቱ ቢያድግም በኮንትሮባንድ እየተሸጠ ነው ተብሏል

እሑድ፣ ነሐሴ 26 2016

በኮንትሮባንድ መበራከት ምክንያት ወርቅ ወደ ባንክ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን በመጥቀስ በወር 30 እስከ 40 ኪ.ግ ወደ ባንክ ይገባ የነበረው ወርቅ በዚሁ ኮንትሮባንድ ምክንያት ወደ 10 እና 15 ኪ.ግ ዝቅ ማለቱን ታውቋል፡፡

የወርቅ ምርቱ ቢያድግም በኮንትሮባንድ እየተሸጠ ነው ተብሏል
የወርቅ ምርቱ ቢያድግም በኮንትሮባንድ እየተሸጠ ነው ተብሏልምስል Ueslei Marcelino/REUTERS

የወርቅ ምርቱ ቢያድግም በኮንትሮባንድ እየተሸጠ ነው ተብሏል

This browser does not support the audio element.

በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የወርቅ ከምችት ይገኝባታል በተባለው ዲማ ወረዳ ወደ ብሔራዊ ባንክ ይገባ የነበረውወርቅ መጠን መቀነሱን የወረዳው አስተዳደር  አመልክተዋል፡፡ በወረዳው  79 የሚደርሱ  ሰዎች ፈቃድ ወስደው  በወርቅ ማምረት ስራ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ እየተሸጠ በመሆኑ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው ወርቅ መጠን በከፍኛ ሁኔታ መቀነሱን  የወረዳው አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኡጁሉ ኡማን  ገልጸዋል፡፡ በ10 ቀናት ውስጥ እያንዳንዱ ማህበር 600 ግራም ወርቅ ወደ ባንክ ማስገባት እንዳለባቸው ማስጠንቀቂያ ለማህበራት መሰጠቱንም የወረዳው አስተዳዳሪ ተናግረዋል፡፡ 
የ17 ወርቅ አምራቾች ፈቃድ ተሰርዟል
በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን ዲማ ወረዳ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወርቅከሚመረትባቸው የጋምቤላ አካባቢዎች አንዱ ሲሆን ከዚሁ ወረዳው ከ3 መቶ  ኪ.ግ በላይ ወርቅ በዓመት ወደ ባንክ ይገባ እንደነበር የወረዳው አስተዳዳሪ አመልክተዋል፡፡ በወረዳው በባህላዊና በአነሰተኛ ወርቅ አምራቾች በኩል ወደ ባንክ የሚገባው ወርቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኡጁሉ ኡማን ለዶይቼቨለ ተናግሯል፡፡ በአካባቢው  በኮንትሮባንድ መበራከት ምክንያት ወርቅ  ወደ ባንክ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን በመጥቀስ በወር 30 እስከ 40 ኪ.ግ ወደ ባንክ ይገባ የነበረው ወርቅ በዚሁ ኮንትሮባንድ ምክንያት ወደ 10 እና 15 ኪ.ግ ዝቅ ማለቱን ገልጸዋል፡፡ 

በአካባቢው  በኮንትሮባንድ ምክንያት  በወር 30 እስከ 40 ኪ.ግ ወደ ባንክ ይገባ የነበረው ወርቅ ወደ 10 እና 15 ኪ.ግ ዝቅ ማለቱንምስል LUIS TATO/AFP


በዲማ ወረዳ ከ100 በላይ ሰዎች በወርቅ ምርት ላይ ለመሰማራት ፈቃድ መውሰዳቸው የተነገረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 79 የሚደርሱ አምራቾች በስራ ላይ እንደሚገኙ አቶ ኡጁሉ አብራርተዋል፡፡ በመስኩ የተሰማሩ ግለሰቦች ከባህላዊ አሰራር በተጨማሪ ዘመናዊ ማሽኖች መጠቀም ቢጀምሩም የተገኘው የወርቅ መጠን አለመጨመሩን በመግለጽ በዚህ ዓመት17 አምራቾች ፈቃዳቸው መሰረዙን አመልክተዋል፡፡
በወረዳው ወርቅ አምራቾች ከባህላዊ ወርቅ ማውጣት ስራ ወደ ዘመናዊ አሰራር ከተሸጋገሩ ወዲህ በርካታ ወርቅ እየተገኘ እንደሆነ የነገሩን አንድ የወረዳው አስተዳደር ባለሙያ አብዛኛው የተመረተው ወርቅ ወደ ባንክ እንደማይገባ ገልጸዋል፡፡ በ2014 ዓ.ም ከወረዳው ከ1ሺ በላይ ኪ.ግ ወርቅ መገኘቱንና ወደ ባንክ መባግን ጠቁመው በወረዳው ከፍተኛ የወርቅ ክምችት እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ 
በዲማ ወረዳ በያዝነው 2016 ዓ.ም 287 ኪ.ግ በላይ ወርቅ ወደ ብሐየራዊ ባንክ መግባቱን የወረዳው አስተዳደር መረጃ ያመለክታል፡፡ በወረዳው  ከሚገኙው ከፍተኛ ወርቅ ክምችት አንጻር 1000 ኪ.ግ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት ታቅዶ እንደነበር የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኡጁሉ ኡማን አስታውቋል፡፡ 
ነጋሳ ደሳለኝ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW