1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኮንጎ ቀውስ የምስራቅና ደቡባዊ አፍርቃ አገር መሪዎች ጉባኤ

ዓርብ፣ ጥር 30 2017

የምስራቃዊና ደቡባዊ አፍሪቃ አገሮች መሪዎች በኮንጎ ሪፑብሊክ በተክሰተው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ለመምከር ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ ተሰብስበዋል። በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው አማጺ ቡድን በምስራቃዊው ኮንጎ በክፈተው ወታደራዊ ጥቃት በሺ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል አፈናቅሏልም።

DR Kongo |  M23-Soldaten in Goma
ምስል፦ ALEXIS HUGUET/AFP via Getty Images

በኮንጎ ቀውስ የምስራቅና ደቡባዊ አፍርቃ አገር መሪዎች ጉባኤ

This browser does not support the audio element.

የምስራቅና ደቡባዊ አፍርቃ አገሮች መሪዎች ጉባኤ በኮንጎ ቀውስ ላይ

የምስራቃዊና ደቡባዊ አፍሪቃ አገሮች መሪዎች በጎንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ በተክሰተው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ለመምከር ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ ተሰብስበዋል። M 23 የተሰኘውና በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው አማጺ ቡድን ባለፈው ሳምንት በምስራቃዊው ኮንጎ የኪቩ ግዛት በክፈተው ወታደራዊ ጥቃት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ያሏትን የጎማ ከተማን በመቆጣጠርና ይዞታውን በማስፋት በሺ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉና ማፈናቀሉ ተገልጿል።

የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ክስና የሩዋንዳ ማስተባበያ

 ኮንጎ ለጥቃቱ በዋናነትሩውንዳን ተጠያቂ አድርጋለች። ሩዋንዳ ክሱን ብታስተባብልም ምራባውያንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግን ሩዋንዳ ከ 4000 በላይ ወታደሮችን በጎንጎ ግዛት እንዳሰማራች በማመን፤ በአስቸኳይ ወታደሮቿን እንድታሰውጣና አማጽያኑን ክመደገፍ እንድትቆጠብ  ነው የጠየቁት። የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በበኩላቸው፤ ወታደሮቻቸው በጎንጎ አለመገኘታቸውን ብቻ ሳይሆን M 23 የሚባለው ቡድንና አባሎቹ፤ ከሩዋንዳ የሄዱና የሜደገፉ እንዳልሆነ ነው የሚከራከሩት፤

“ በመሬት ላይ እየተዋጉ ያሉት ሀይሎች ከሩዋንዳ የመጡ ሳይሆን በስደት ከነበሩበት ኡጋንዳ የመጡ ናቸው” በማለት የጎንጎ ችግር የእራሷ የውስጥ ችግር እንጂ የሩዋንዳ አለመሆኑን ገልጸዋል።  ይህ የፖለቲካ ውዝግብና ግጭት ከሁለቱ አገሮች አልፎ አካባቢውን ሌላ የጦር አውድማ እንዳያደርገው አስግቷል።

የስብሰባው አላማና አይነተኛ አጀንዳው

 ሩዋንዳንና ኮንጎንጨምሮ ስምንት የምስራቅ አፍርካ አገሮችና ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎን ጨምሮ 16 አባላት ያሉት የደባዊ አፍሪቃ አገሮች መሪዎች ስብሰባ በታንዛኒያ የተጠራውም በዋናነት ለዚህ ቀውስ መፍሄ ለመሻትና፤ ያንዛበበውን የጦርነት ዳመና ለመግፈፍ ነው ተብሏል። በስብሰባውም የሁለቱም ማለት የሩዋንዳና ዴሞክራቲምክ ሪፑብሊክ ኮንጎ መሪዎች ክዛሬው የሚኒስትሮች ጉባኤ ማግስት በሚደረገው የመሪዎች ስብሰባ እንደሚገኙ ተረጋግጧል። መሪዎቹ በስብሰባቸው ሊያተኩሩበትና ቅድሚያ ሊሰጡት የሚገባው አጀንዳ የትኛው መሆን እንዳለበት በናይሮቢ ስታትሞር ኒቨርርስቲ የዓለማቀፍ ጥናት መምህሩ ዶክተር ኢድጋር ጊቱዋ፤ “የዚህ ስብሰባ ቁጥር አንድ አጀንዳ ሊሆን የሚገባው የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ በማድረግ የጠመንጃ ጩኸትን ማስቆም ማስቻል ነው” በማለት  የጠመንጃ ላንቃ ሳይዘጋ ሌላ ነገር ሊሰራ እንደማይችል አስገንዝበዋል።

የዴሞክራቲክ ኮንጎ ቀዉስ - M23 አማጽያን ምስል፦ Belga MagAFP/Getty Images

የሰላሙ ተስፋ

ይሁን እንጂ በለንደን የክዊን ዩንቭርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ሩዊበን ላፍማን እንደሚሉት፤ ሩውናዳም ሆነች የምትደግፈው አማጺ ቡድን በአሁኑ ወቅት የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ ለመድረስ ፍላጎት የላቸውም። የተክሱ ማቆም ስምምነት ማድረግ የሚፈልጉት በነሱ ቅድመ ሁኒታ ብቻ ነው። በአሁኑ ወቅት ግን ተኩስ የማቆም ስትርቴጂካዊም ሆነ ስልታዊ ፍላጎት የላቸውም። የበለጠ መግፋት ነው የሚፈልጉት፣ የዴሞክርቲክ ኮንጎ ሰራዊት እንደማይመክታቸው ተረድተዋል” በማለት ሁኔታው ለጎንጎ ጥሩ እንዳልሆነና ፕሬዝዳንት ሺሴኬዲና ሰራዊታቸው ብዙ ስራ እንደሚጠብቃቸው አስታውቀዋል።

ሩዋንዳ በኮንጎ ላይ ያላት የኢኮኖሚ ፍላጎት

ፎቶ ማህደር፤ የምስራቃዊና ደቡባዊ አፍሪቃ አገሮች መሪዎች ስብሰባ በዩጋንዳምስል፦ Hajarah Nalwadda/Xinhua/imago images

እ.እ.እ በ1994 የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመባት ሩዋንዳ ጠንካራ ስራተ መንግስት በመመስረትና በልማት አፈጻጸም ተጠቃሽ ብትሆንም ከጎረቤቶቿ ጋር ጥሩ ግንኑነት ባለመፍጠርና  በተለይ በዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ኮንጎጣልቃ በመግባት ግን ትወቀሳለች። ሩዋንዳ  በጎንጎ የምታደርገው ጣልቃ ገብነት የኢኮኖሚ ገጽታም እንዳለው የሜነገር ሲሆን M 23 ቡድን በወር አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የወርቅና ኮቶን ማዕድናት ከኮንጎ ወደ ሩውንዳ እንደሚያስወጣ የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመለክት የጠቆሙት በክራይሲስ ግሩፕ የታላቁ ሀይቅ አካባቢ  ፕሮጀክት ዳይሪክተር ሪቻርድ ሞንክሪፍ ናቸው።

ሩዋንዶች  በአጠቅላይ ሲታይ ሊኮኖሚም ሆነ ለጸጥታ በኪቩ አካባቢ ተሰሚና ተጾኖ ፈጣሪ ሆኖ መቀጠልን ዋና  ፖሊስያቸው አድርገው  ወስደውታል በማለት ሩዋንዳና ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ በቀላሉ መቀራረብ መቻላቸውን አጠይቀዋል።  

በሩዋንዳ ላይ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ጫና አይደረግም ስለመባሉ

የዴሞክራቲክ ኮንጎ ቀዉስ - M23 አማጽያን ምስል፦ Hardy Bope/AFP/Getty Images

የዓማቀፉ ማህብረሰብም ሩዋንዳ አለማቀፍ ህጎችን በመጣስ በሌሎች አገሮች ጣልቃ ስተገባ አይቶ እንዳላየ ያልፋታል በመባል ይወቀሳል። በአሁኑ ወቅትም የአውሮጳ ህብረት ከሩዋንዳ ጋር የፈረመውን የመእድናት ንግድ ውል እንዲስርዝ ግፊት እይተደረገ ነው። ሆኖም ግን ሩዋንዳ በአፍርካ ከፍተኛ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት የምታዋጣ መሆኑ፤ በሞዛምቢክ ጂህዲስቶችን በመዋጋት የፈርንሳይን ጥቅም ማስጠበቋ፣ ከአውሮጳ የሚባረሩ ስደተኖችን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆኗ፤ የብድርና ልማት ገንዘብ አጠቃቀሟ የተሻለ መሆኑና ከሁሉም በላይ ግን ምራባውያን  የ1994ቱ የዘር ማጥፋት ወንጃል እንዳይፈጸም ባለማድረጋቸው በሚሰማቸው የጥፋተኘነት ወንጀል ምክኒያት፤ በሩዋንዳ ላይ የጠበቀ እርምጃ ክመውሰድ እንዲቆጠቡ እዳደረጋቸው ነው በብዙዎች የሚታመነው።

ገበያው ንጉሤ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW