በወለጋ የመጓጓዣ ዋጋ መናር
ረቡዕ፣ ሐምሌ 16 2017
ማስታወቂያ
በወለጋከዶምቢዶሎ ከተማ ወደ ነቀምት እንዲሁም ወደ ጊምቢ ለመጓጓዝ ከመደበኛ ታሪፍ በላይ ዋጋ እንደሚከፍሉ ነዋሪዎች በምሬት ይናገራሉ። ከዚህ ቀደም ዶቼቬለ ባቀረበው ዘገባ ዋጋው ይስተካላል ተብሎ ነበር ፤ሆኖም አሁንም ዋው አልቀነሰም፡፡ ለአብነት ያህል ከደምቢዶሎ ጊምቢ መደበኛ የመጓጓዣ ዋጋ 400 ብር ነው ይሁንና ተጓዦች አሁን እንደሚሉት አሁን 650 ብር ነው የሚከፍሉት፡፡
ለዚህም የነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ የአቅርቦት ችግር እና እጥረት በምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልካማሺ ዞን ደግሞ የመንገድ ችግር እና ከክረምት ጋር ተያይዞ የወንዝ ሙላት በትራንስርት አገልግሎት ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው። በነዚህ አካባቢዎች ስላለው የመጓጓዣ ችግር የነዋሪዎች ሮሮ እና መፍትሄ ስለሚባለው የአሶሳውን ወኪላችንን ነጋሳ ደሳለኝን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ