1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፍልሰትአውሮጳ

በወሲባዊ ጥቃቶች ተበይኖበት ከብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ የተባረረው ሀዱሽ ገብረሥላሴ ቅባቱ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 19 2018

የብሪታንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ በስህተት ከታሰረበት ከተለቀቀ፣48 ሰዓታት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ እሁድ ዳግም የታሰረው ተገን ጠያቂው ሀዱሽ ገብረ ሥላሴ ከብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ መባረሩን ዛሬ አስታውቋል። በሌላ በኩል ብሪታንያ በሆቴሎች ውስጥ የምታኖራቸውን ተገን ጠያቂዎች ወደ ቀድሞ ወታደራዊ ጦር ሰፈሮች ለማዛወር ማቀዷን አስታውቃለች።

በብሪታንያ በሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃቶችና ትንኮሳ በመፈጸም የተፈረደበት ሀዱሽ ገብረ ሥላሴ ቅባቱ
በብሪታንያ በሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃቶችና ትንኮሳ በመፈጸም የተፈረደበት ሀዱሽ ገብረ ሥላሴ ቅባቱ ምስል፦ Essex Police/AFP

በወሲባዊ ጥቃትና ትንኮሳ ተበይኖበት ከብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ የተባረረው ሀዱሽ ገብረ ሥላሴ ቅባቱ

This browser does not support the audio element.

በሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃቶችና ትንኮሳ በመፈጸም የተፈረደበት ሀዱሽ ገብረ ሥላሴ ቅባቱ ዛሬ ወደ ኢትዮጲያ ተጠረዘ ፤ ብሪታንያ ተገን ጠያቂዎች ወደ ቀድሞ ወታደራዊ ጦር ሰፈሮች ልታዛውር ነው
የብሪታንያ መንግሥት በሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃቶችና ትንኮሳ በመፈጸም የተፈረደበትን ሀዱሽ ገብረ ሥላሴ ቅባቱን ወደ ኢትዮጲያ መጠረዙን ዛሬ አስታወቀ።

የብሪታንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት፣ በስህተት ከታሰረበት ከተለቀቀ ፣48 ሰዓታት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ እሁድ ዳግም የታሰረው ሀዱሽ ኢትዮጵያ መድረሱን ዛሬ አስታውቋል። በአንዲት የ14 ዓመት ልጃገረድና በአንዲት አዋቂ ሴት ላይ የወሲብ ጥቃትና ትንኮሳ በመፈጸም አንድ የብሪታንያ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የጥፋተኝነት ብይን ያሳለፈበት የ38 ዓመቱ ሀዱሽ ከተወሰነበት የአንድ ዓመት እሥራት ውስጥ አንድን ወር በእስር ቤት አሳልፎ ነበር። 

በስህተት ከእስር ቤት የተለቀቀው ሀዱሽ ገብረ ሥላሴ እሁድ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በለንደን ፖሊስ ተይዞ ሲወሰድ ምስል፦ News Licensing/IMAGO

በሌላ በኩል ብሪታንያ በሆቴሎች ውስጥ የምታኖራቸውን ተገን ጠያቂዎችን ወደ ቀድሞ ወታደራዊ ጦር ሰፈሮች ለማዛወር ማቀዷን አስታውቃለች። ሁለት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ጦር ሰፈሮች በጊዜያዊነት ቁጥራቸው 900 ለሚደርስ ወንድ ስደተኞች ማቆያ እንደያገለግሉ መታቀዱን የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር  ቃል አቀባይ አስታውቀዋል።

ይሁንና አሁንለተገን ጠያቂዎች ማቆያ ለታሰቡት የቀድሞ የጦር ሰፈሮች ማደሻ ሆኖ ለሌሎች አገልግሎቶች የሚያስፈልገው ገንዘብ ለሆቴሎቹ ይወጣ ከነበረው የሚበልጥ መሆኑ ማነጋገሩ አልቀረም። መንግሥት ግን የሚያስወጣው ገንዘብ ቢበዛም የህዝብን ቅሬታ ለማቃለል እስከረዳ ድረስ አያሳስበኝም ብሏል።

ስለሀዱሽ ገብረሥላሴ ቅባቱ ወደ ኢትዮጵያ መጠረዝና፣ ብሪታንያ ተገን ጠያቂዎች ወደ ቀድሞ ጦር ሰፈሮች ልታዛውር ማቀዷን በተመለከተ የለንደኑን ወኪላችንን ድልነሳ ጌታነህን በስልክ  አነጋግረነዋል።

ድልነሳ ጌታነህ 

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW