በወቅታዊ ጉዳዮች የውጭ ጉዳይ መግለጫ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 14 2013
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን እና በክልሉ ተፈጽሟል የተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ ፍላጎቷ መሆኑን ለአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ መግለጿን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዐስታወቀ። ይሁንና ከተለያየ ወገን የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት የሚጋፉ ነገሮችን በተመለከተ የሚቀርቡ ክሶች ተቀባይነት እንደሌላቸው መንግስት አቋሙን ማሳወቁንም ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል። የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር አሁን ለጊዜው ቢቋረጥም አራተኛ አደራዳሪ ወገን ይግባ የሚለውን የሁለቱ የታችኛው ተፋሰስ አገራትን ፍላጎት አሁንም ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ዐስታውቃለች።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ