በዓባይ ጉዳይ፦ «ኢትዮጵያ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች»
ዓርብ፣ የካቲት 6 2012
ማስታወቂያ
ስለ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2012 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ የረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጀት ሲካሄድ የነበረው ውይይት ያለስምምነት መቋጨቱ ተገልጧል። ውይይቱ በኢትዮጵያ፤ በሱዳን እና በግብጽ መካከል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ የረቂቅ ስምምነት ሰነድ ለማዘጋጀት ነበር የተካሄደው። አንዳንድ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች፦ በድርድሩ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ እና የዓለም ባንክ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር በመኾን ኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ጥረው ነበር ብለዋል። በአባይ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባች ደግሞ የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ያነጋገራቸው ዶክተር ዓለማየሁ አረዳ ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ