ስለደመወዝ ጭማሪው የሕዝብ አስተያየት
ረቡዕ፣ ነሐሴ 14 2017
ማስታወቂያ
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ መንግስት ከመጪው መስከረም ጀምሮ በተለይ ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደርግ በይፋ አስታውቋል፡፡ይህ የደመወዝ ጭማሪ ለሠራተኛው መልካም ከመሆኑም በላይ አንገብጋቢ ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፤ ነገር ግን የደመወዝ ጭማሪ ብቻውን በቂ አለመሆኑን በአስተያየታቸው ገልጸዋል፡፡
የደመወዝ ጭማሪው ለዋጋ ንረት ምክንያት ሆኖ ማህበረሰቡ ላይ ተጨማሪ ጫና አንዳይከሰት በአቅርቦትና መሰል ስራዎች ላይ ተገቢ ቁጥጥር ላይ ይበልጥ መሰራት እንዳለበት የነዋሪው አብይ ጥያቄ ነው፡፡
ከደመወዝ ጭማሪው ይልቅ የግብር እና ተያያዥ ወጪውች ቅነሳ እና የሰራተኛው ጥቅማጥቅም ላይም መስራት አስፈላጊ መሆኑን ነዋሪዎቹ አስተያየት ሰጥተዋል። ሥዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ተከታዮቹን የህዝብ አስተያየቶች አሰባስቧል።
ሥዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ልደት አበበ