1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታገዱት የወርቅ አምራች ማህበራት

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 2 2015

ማህበራቱ የታገዱት በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት በዓመት ከ1 ኪ/ግራም በላይ ወርቅ ማቅረብ ሲገባቸው ባl,ማቅረባቸውና የቁፋሮ ቦታዎች ባለማልማታቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ተናግረዋል።ክልሉ በ2015 በጀት ዓመት 450 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ ቢያቅድም ማቅረብ የቻለው ግን 67 ኪሎ ግራም ብቻ ነውም ብለዋል

በአፈጻጸም ግምገማው መሠረት በብሔራዊ ባንክ የተቀመጠውን መመሪያ ተፈጻሚ ሳያደርጉ ቀርተዋል በተባሉ 21 የወርቅ አምራች ማህበራት ላይ  የእግድ እርምጃ መወሰዱን ነው ዋና  ዳይሬክተሩ ለዶቼ ቬለ DW የተናገሩት   
የኤጀንሲው የሥራ ሃላፊዎች እንዳሉት በክልሉ 34 የሚሆኑ የወርቅ አማራች ማህበራት ቢኖሩም አብዛኞቹ ውል በገቡት መሠረት እየተንቀሳቀሱ አይደለም ፡፡ ለዚሁ ተግባር የተቋቋመው የክልሉ ግብረሀይል ሰሞኑን ማህበራቱ በወርቅ ምርትና ግብይት ዙሪያ ያከናወኑትን የሥራ አፈጻጸም መገምገሙን የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ሰጠኝ ገልጸዋል ፡፡  ምስል Karl Mathis/KEYSTONE/dpa/picture alliance

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የታገዱት የወርቅ አምራች ማህበራት

This browser does not support the audio element.

በ “ከመመሪያ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል “ ያላቸውን 21 የወርቅ አምራች ማህበራት ማገዱን የክልሉ ውሃ ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ አስታወቀ ፡፡ የኤጀንሲው የሥራ ሃላፊዎች እንዳሉት በክልሉ 34 የሚሆኑ የወርቅ አማራች ማህበራት ቢኖሩም አብዛኞቹ ውል በገቡት መሠረት እየተንቀሳቀሱ አይደለም ፡፡ ለዚሁ ተግባር የተቋቋመው የክልሉ ግብረሀይል ሰሞኑን ማህበራቱ በወርቅ ምርትና ግብይት ዙሪያ ያከናወኑትን የሥራ አፈጻጸም መገምገሙን የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ሰጠኝ ገልጸዋል ፡፡ በአፈጻጸም ግምገማው መሠረት በብሔራዊ ባንክ የተቀመጠውን መመሪያ ተፈጻሚ ሳያደርጉ ቀርተዋል በተባሉ 21 የወርቅ አምራች ማህበራት ላይ  የእግድ እርምጃ መወሰዱን ነው ዋና  ዳይሬክተሩ ለዶቼ ቬለ DW የተናገሩት   
ጥቁር ገበያ በደቡብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን የሚገኘው ከሰል ማዕድን
በማህበራቱ ላይ የእግድ እርምጃው የተወሰደው በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት በዓመት ከአንድ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ማቅረብ ሲገባቸው ባማቅረባቸውና የወሰዷቸውን የቁፋሮ ቦታዎች ባለማልማታቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ተናግረዋል ፡፡ ክልሉ በ2015 በጀት ዓመት 450 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ ቢያቅድም  ማቅረብ የቻለው ግን 67 ኪሎ ግራም ብቻ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ይህም አንዳንድ ማህበራት በጥቁር ገበያ የመሳተፍ አዝማሚያን በማሳየታቸው ነው ብለዋል፡፡
የማህበራቱ ተግዳሮቶች 
የእግድ እርምጃ ተወስዶባቸዋል የተባሉት ማህበራት አመራሮች በበኩላቸው የኤጀንሲው ውሳኔ አግባብነት  የጎደለውና በሺህዎች የሚቆጠሩ የማህበሩ አባላትን ያለሥራ ያስቀረ ነው ብለዋል ፡፡  የመሠረተ ልማት አለመሟላትና በአካባቢው የሚስተዋለው የፀጥታ ችግር በዕቅዳቸው ልክ  እንዳይንቀሳቀሱ እንዳደረጋቸው  ጂ.ፒ.ዜድ የተባለው የወርቅ አምራች ማህበር ሊቀመንበር አቶ እሸቱ ገሴ ገልጸዋል፡፡በደቡብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን የሚገኘው ከሰል ማዕድን
አብዛኞቹ ማህበራት ለወርቅ ምርት አገልግሎት ክረምት ላይ የወንዝ ውሃ ቢጠቀሙም በበጋ ወቅት ግን ያን ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን የጠቀሱት አቶ እሸቱ “ወደ ወርቅ ማውጫ ሥፍራዎች የሚያስገቡ መንገዶችም ለተሽከርካሪ አስቸጋሪ ከመሆናቸው የተነሳ ውሃ ከሌላ ቦታ ለመጓጓዝ የሚታሰብ አይደለም ፡፡፡ እነኝህን ችግሮች ተቋቁመን ለማምረት ብንሞክረም የፀጥታው ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም ፡፡  በሠራተኞች ላይ በተደጋጋሚ የግድያና የዘረፋ ወንጀሎች ያጋጥማሉ ፡፡ ኤጀንሲው የእግድ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ማህበራቱን ያሉባቸውን ችግሮች  ከግምት ማስገባት ነበረበት “ ብለዋል  ፡፡
ወደ ምርት የመመለስ ተስፋ በደቡብ ምዕራብ ክልል የትምህርት ማስረጃን ያጭበረበሩ ላይ ርምጃ ተወሰደ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ሰጠኝ ማህበራቱ “ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው እየሠራን የምንገኘው “ ያሉት ትክክል ነው ይላሉ ፡፡ በአካባቢው የመሠረተ ልማትና የፀጥታ ችግሮች መኖራቸው እውነት መሆኑን የተናገሩት አቶ ገብረማርያም “ በዚህ መነሻ ማህበራቱ ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች በመመርመር ወደ ሥራ ሊመለሱ የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች እያጤንን እንገኛለን ፡፡  በአሁኑወቅትም በዞን ፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ከአምራች ማህበራቱ ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር እየተንቀሳቀስን እንገኛለን  “ ብለዋል፡፡ 
ሸዋንግዛው ወጋየሁ 
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ
 

በማህበራቱ ላይ የእግድ እርምጃው የተወሰደው በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት በዓመት ከአንድ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ማቅረብ ሲገባቸው ባማቅረባቸውና የወሰዷቸውን የቁፋሮ ቦታዎች ባለማልማታቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ተናግረዋል ፡፡ ምስል Keystone/dpa/picture alliance
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW