1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በደቡብ ሱዳናውያን መካከል በተከሰተ ግጭት ኢትዮጵያኑ ጉዳት ደረሰባቸው

ዓለምነው መኮንን
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 25 2017

የሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ተቃዋሚ (SPLM in Oppsition) የተባለው የደቡብ ሱዳን አማፂ ኃይልና የደቡብ ሱዳን የመንግስት ወታደሮች ኢትዮጵና ደቡብ ሱዳን በሚዋሰኑበት የጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ ባለፈው ረቡዕ ባካሄዱት ጦርነት የላሬ ወረዳ ወና አስተዳዳሪ አቶ ቶክ ሞንግ መቁሰላቸውን ህክማና ጣቢያ ሆነው ለዶይቼ ቬሌ ተናገሩ

Karte Äthiopien Südsudan Gambella Englisch

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ጉዳት አደረሱ

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ሱዳናውያን መካከል በተከሰተ ግጭት ኢትዮጵያኑ ጉዳት ደረሰባቸው

የሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ተቃዋሚ (SPLM IO) የተባለው የደቡብ ሱዳን አማፂ ኃይልና የደቡብ ሱዳን የመንግስት ወታደሮች ኢትዮጵና ደቡብ ሱዳን በሚዋሰኑበት የጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ ባለፈው ረቡዕ ባካሄዱት ጦርነት የላሬ ወረዳ ወና አስተዳዳሪ አቶ ቶክ ሞንግ መቁሰላቸውን ህክማና ጣቢያ ሆነው ለዶይቼ ቬሌ ተናገሩ።

የጋምቤላ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ አሁን በኢትዮጵያ ግዛት የሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች ጦር እንደሌለ አረጋግጠዋል፡፡

የሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ተቃዋሚ (Sudan People’s Liberation Movement in Opposition) የተባለው አማፂ ኃይልና የደቡብ ሱዳን የጦር ኃይል ባለፈው ረቡዕ በኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን አዋሳኝ በሆነው የጋምቤላ ክክል ላሬ ወረዳ አቅራቢያ ባደረጉት ውጊያ በኢትዮጵያውያን ላይ ጉዳት መድረሱን የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ኡጉላ ኡጁሉ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ኃይሎች በሚያደርጉት ውጊያ ወደ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ  ሸሽተው ድንበር የሚሻገሩ የታጠቁ ኃይሎች የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪን በማቁሰል ቤቶችንም አቃጥለዋል ብለዋል፣ ሆኖም አሁን የሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ተቃዋሚ ተዋጊዎችም ሆኑ የደቡብ ሱዳን የመንግስት ጦር  ኃይሎች በኢትዮጵያ ግዛት እንደማይገኙ ኮሚሽነር ኡጋላ አመልክተዋል፡፡

ለቱ ኃይሎች በሚያደርጉት ውጊያ ወደ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ  ሸሽተው ድንበር የሚሻገሩ የታጠቁ ኃይሎች የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪንምስል፦ dapd

በጋምቤላ ክልል አቦቦ ወረዳ በደረሰው ጥቃት የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉ

ወገባቸው አካባቢ በጥይት ተመትተው በጋምቤላ የመጀመሪያ ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙት የላሬ ወረዳ ወና አስተዳዳሪ አቶ ቶክ ሞንግ አማፅያኑ አፈግፍገው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ክግቡ በኋላ የደቡብ ሱዳን ኃይሎች ተከትለው በመግባት ህዝቡን ለማረጋጋት ወደ ቦታው በተንቀሳቀሱ ኢትዮጵያውያን ፖሊሶችና በራሳቸው በአስተዳዳሪው ላይ ተኩስ መከፈታቸውን ገልጠዋል፣ ሂደቱን እንዲህ ያስረዳሉ፣

“...መነሻው SPLM-in Opposition (IO)ነው፡፡ የእኛ ፖሊሶች (ኢትዮጵያውያን) የኢትዮጰያን ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ ማንነታቸውን በማሳወቅ ህዝቡ እንዳደናገጥ በማረጋጋት ላይ ነበሩ፣ ዓላማችንም ህዝቡ ተደናግሮ በማይመለከተው ጦርነት እንዳገባ ለማድረግ ነበር፣ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ግን ባላሰብነው መንገድ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ተኩስ ከፈቱ፣ እኛ ደግሞ ፈርተን ሳይሆን  ከነርሱ ጋር ለመዋጋት ዓላማ ስለሌለን ወደ ኋላ መሸሽ ጀመርን፣ እኔም ማንደር ከሚባል ቦታ ላ በጥት ተመትቸ ቆሰልኩ አሁን በጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በህክምና ላይ ነኝ፡፡” ብለዋል፡፡

ወደ ጋምቤላ የሚሰደዱ ደቡብ ሱዳናዉያን ቁጥር እየጨመረ ነዉ ተባለ

የሳልቫኪር ወታደሮች በኢትዮጵያውያን ላይ ተኩስ ከከፈቱና  አስተዳዳሪውም ከቆሰሉ በኋላ ህብረተሰቡ ቁጣውን ባማሰየቱ ወታደሮቹ ከኢትዮጰያ ግዛት መውጣታቸውን አቶ ቶክ አረጋግጠዋል፡፡

አዲስ አበባ ለሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኢምባሲ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ አስተያየት እንዲሰጠን በኢሜል ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

የተለያዩ የታጠቁ ኃይሎች በተለያዩ ጊዜዎች ከደቡብ ሱዳን እየተሻገሩ በጋምቤላ ክልል አንዳንድ ካባቢዎች ጥቃት ሲፈፅሙ እንደነበር በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW