1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ አፍሪቃ የሱቅ ባለቤት በሆኑ መጤዎች ላይ የተሰነዘረዉ ጥቃት እና ስጋቱ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 17 2016

በደቡብ አፍሪቃ ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ የሸቀጥ ባለሱቅ የዉጭ ዜጎች ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ፍርሃት ዉስጥ ይገኛሉ። ጥቃቱን የሰነዘረዉ ዱዱላ የተባለዉ ፀረ-ስደተኛ ቡድን ነዉ። በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ የሸቀጥ ሱቆች ያልዋቸዉ በርካታ ኢትዮጵያዉያን አንድም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘባቸዉን ተዘርፈዋል፤ አልያም ሱቃቸዉን ዘግተዉ ለመሸሽ ተገደዋል።

ደቡብ አፍሪቃ: በፀረ-ስደተኛ ቡድን የዉጭ ዜጎች ላይ ጥቃት
ደቡብ አፍሪቃ: በፀረ-ስደተኛ ቡድን የዉጭ ዜጎች ላይ ጥቃት ምስል AP

በርካታ ኢትዮጵያዉያንን ባለሱቆች በሚሊዮን የሚያወጣ ገንዘፍ ተዘርፈዋል፤ ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ ፍርሃትም ላይ ናቸዉ።

This browser does not support the audio element.

በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ የሸቀጥ ባለሱቅ የዉጭ ዜጎች ላይ ባለፈዉ ሳምንት በፀረ ስደተኛ አቀንቃኞች ጥቃት ከተሰነዘረባቸው በኋላ ፍርሃትና በቁጣ ዉስጥ ይገኛሉ። ጥቃቱን አቀናብሮ የሰነዘረዉ ዱዱላ የተባለ የታወቀ ፀረ-ስደተኛ ቡድን ነዉ። በደቡብ አፍሪቃ በተለያዩ አካባቢ እና ከተሞች የሚገኙ በዉጭ ሃገራት ዜጎች ባለቤትነት  ስር የሚገኙ ትናንንሽ የሸቀጥ ሱቆች ተዘግተዋል ። ከባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ እነዚህ ሱቆች የተዘጉት ዱዱላ የተባለዉ ቡድን በሱቆቹ ላይ ጥቃት እና ወረራ ማካሄድ ከጀመረ በኋላ ነዉ።

ይህ ፀረ-ስደተኛ የሆነ ቡድን በሱቆቹ ላይ ወረራ የጀመረዉ በሱቆቹ ዉስጥ ለአደጋ የሚያጋልጥና ለጥቅም የሚዉሉበት ቀነ ገደብ ያለፈበት የምግብ ውጤት በመሸጡ ነዉ ሲል ምክንያቱን አቅርቧል። አንዲት የዚምባቤ ተወላጅዋ ባለሱቅ፤ ጥቃቱ ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ ስትል ትናገራለች።በደቡብ አፍሪቃ የቀጠለው የውጭ ዜጎች ጥቃት እና የሽብር ስጋት በሶማሊያ

«የዱዱላ አባላት፤ የውጭ ዜጎች የንግድ ድርጅቶችን ለማስተዳደር፤ ፈቃድ ለምን ተሰጣቸው ከሆነ ጥያቄዉ ሄደዉ መንግሥትን ወይም የጉዳዩን ባለቤት የሆነዉን ሚስቴር ማነጋገር ይችላሉ።" የዚህ ውዝግብ ዋና ማዕከል የሆነዉ የውጭ ዜጎች ንብረት ከሆኑ አነስተኛ ሱቆች የተገዙ ሸቀጦችን ከበሉ በኋላ አራት ልጆች ሞቱ የተባለበት ሁለት አሳዛኝ ክስተቶች ናቸዉ ተብሏል።የኢትዮጵያውያኑ ፈተና በደቡብ አፍሪቃ 

የዱዱላ ኦፐሬሽን አባላት በሱቆች ውስጥ እንዲህ ዓይነቱን ወረራ የማካሄድ ሥልጣን እንደሌላቸው ቢቀበሉም ኃላፊነት የሚሰማቸው ባለ ሥልጣናት ቸልተኞች በመሆናቸዉ በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተናል ይላሉ።

"ዓላማችን ማኅበረሰቡ አደገኛ የሆኑ ምግቦችን ከእነዚህ ትናንሽ ሱቆች እንዳይገዛ እና እንዳይበላ ለመከላከል እንደሆነ ግልጽ ነው። አሁን ያለፈባቸዉ የሴቶች የንጽህና መጠበቅያን ጨምሮ የመጠቀምያ ጊዜያቸዉ ያለፈባቸዉ የምግብ ውጤቶችን በተሳካ ሁኔታ ለይተናል።" ይላል አንዱ የዱዱላ አባል። 

ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ በዉጭ ዜጎች ላይ የተሰነዘረዉ ጥቃት

ነዋሪነቱን በደቡብ አፍሪቃ ደርባን ክዋዙሉ ናታል ከተማ ያደረገ እና በዝያዉ ክልል ዉስጥ በሚገኝ ፍትህ ቢሮ ዉስጥ የሚሰራዉ ኮስሞስ ገብረሚካኤል እንደሚለዉ ይህ አይነቱ ዝርፍያ እና የዉጭ ሃገር ዜጎች ጥላቻ በደቡብ አፍሪቃ ምርጫ ሲቃረብ ሆነ ተብሎ የሚደረግ ጉዳይ ነዉ። የመጤ ጠል ጥቃት በደቡብ አፍሪቃ ፤የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር የአፍሪቃ ጉብኝት

በደቡብ አፍሪቃ በቅርቡ በህግ የተመዘገበዉ ዱዱላ የተባለዉ ንቅናቄ፤ በምርጫ  ተወዳድሮ በሃገሪቱ ምክር ቤት ወንበር ለማግኘት ጥረት ላይ ነዉ። ስሙ በራሱ ሲተረጎም «በጉልበት ማስወጣት» የሚል እንደሆን ኮስሞስ ገብረሚካኤል ነግሮናል።  ዶዶላ ባለፈዉ ጥቃቱን ዚምባቤ ተወላጆች ላይ ነበር አሁን ደግሞ ኢትዮጵያዉያን ላይ ነን ብሏል። 

በደቡብ አፍሪቃ የሸቀጥ ሱቅምስል Yeshiel/Xinhua/picture alliance

ይሁንና ዱዱላ የሚባለዉ ቡድን ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ባለሱቆችን ማጥቃት የጀመረዉ አራት ህጻናት ከነዚህ ሱቆች የተገዙ ቀን ያለፈባቸዉ ምግቦችን በልተዉ ነዉ ተብሏል። ይህስ እንዴት ይታያል? ትዮጵያዉያን ታድያ በዚህ ዱዱላ በተባለዉ እና ፀረ የዉጭ ሃገር ዜጎች አራማጅ በሆነዉ ቡድን ምን ያህል ተጎድተዋል?

በመጭዉ የጎርጎረሳዉያን 2024 ዓመት ምርጫን ለማካሄድ ዝግጅቷን የጀመረችዉ ደቡብ አፍሪቃ በማኅበረሰቡ የዉጭ ሃገር ዜጎች ጥላቻ እና የሚነዛ አሉባልታ ስር እየሰደደ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ችግሩ ምርጫዉ እስኪያልፍ ተባብሶ መቀጠሉ አይቀሬ ነዉ የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም ይሁን እና እንዳለፈዉ ጊዜ በዉጭ ዜጎች ላይ የኃይል ጥቃት ብሎም ግድያ እንዳይስፋዳፋ ስጋት አሳድሯል።

ይሁንና ዱዱላ የሚባለዉ ቡድን ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ባለሱቆችን ማጥቃት የጀመረዉ አራት ህጻናት ከነዚህ ሱቆች የተገዙ ቀን ያለፈባቸዉ ምግቦችን በልተዉ ነዉ ተብሏል። ይህስ እንዴት ይታያል? ኢትዮጵያዉያን ታድያ በዚህ ዱዱላ በተባለዉ እና ፀረ የዉጭ ሃገር ዜጎች አራማጅ በሆነዉ ቡድን ምን ያህል ተጎድተዋል?

ስለኢትዮጵያዉያኑ ሙሉ ቃለ ምልልሱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW