በደቡብ ከ62 ሺህ በላይ ሰዎች በወንዝ ሙላት ተፈናቀሉ
ማክሰኞ፣ መስከረም 11 2014![[No title]](https://static.dw.com/image/59253659_800.webp)
ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ ሞልቶ ከ62 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን አፈናቀለ። የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ (DW) እንዳሉት ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ቀሰ በቀስ እየሞላ የመጣው የኦሞ ወንዝ የመኖሪያ ቤቶቻቸውን በመዋጡ በአሁኑ ወቅት በኦሞራቴ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸዋል። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የዳሰነች ወረዳ ባለስልጣናት በበኩላቸው በወንዝ ሙላቱ ከተፋናቀሉት ሰዎች በተጨማሪ ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማትን ጨምሮ 22 የመሰረተ ልማት ተቋማትን ማወደሙን ተናግረዋል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ