1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በደቡብ ክልል ከወከላቸው ህዝብ ጋር መገናኘት እንንዳልቻሉ የህዝብ ተወካዮች አመለከቱ

ዓርብ፣ ነሐሴ 26 2015

“ በድምጹ ከወከለን ህዝብ ጋር አንዳንገናኝ በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ተከለከልን “ ሲሉ በአማሮ ዞን የሚገኙ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት አባላት አመለከቱ ፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት አባልነት መቀመጫን ያገኙት የኢዜማ ፓርቲን በመወከል በ2013 ዓ/ም በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ አማካኝነት ነው ፡፡

Äthiopien l Verwaltungsbüro von Amaro Special Wereda
የአማሮ ልዩ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ምስል፦ Shewangizaw Wehgayehu/DW

የአማሮ ዞን የህዝብ ተወካዮች ቅሬታ

“ በድምጹ ከወከለን ህዝብ ጋር አንዳንገናኝ በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ተከለከልን “ ሲሉ በአማሮ ዞን የሚገኙ  የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት አባላት አመለከቱ ፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት አሁን ያሉበትን የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት አባልነት መቀመጫን ያገኙት የኢትዮጵያ ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ፓርቲን በመወከል  በ2013 ዓም በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ አማካኝነት ነው  ፡፡ከደቡብ ክልል የተነጠሉት ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል ለመደራጀት የሚያስችላቸውን መሥራች ጉባዔውን ማካሄድ ጀመሩ።

በውክልናቸው መሠረት በአማሮ ዞን ከኮሬ ሕዝብ ጋር ውይይት ለማድረግ ወደ አካባቢው ቢመጡም ከመረጣቸው ህዝብ ጋር ሊገናኙ እንዳልቻሉ የህዝብ ተመራጮቹ ተናግረዋል፡፡  ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ዞኑን የሚያስተዳድሩት የገዢው ፓርቲ ባለሥልጣናት የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ውይይቱ እንዳይካሄድ በመሥራታቸው ነው  ብለዋል ፡፡  

በደቡብ ክልል የወከለንን ህዝብ ቀርበን ማነጋገር አልቻልንም ሲሉ አንዳንድ የህዝብ ተወካዮች አመለከቱ። ተወካዮቹ እንዳሉት በወከላቸው ህብረተሰብ ውስጥ የሚታዩ ሁለንተናዊ ችግሮችን ለማነጋገር ያደረጉት ጥረት በአካባቢው ባለስልጣናት ተሰናክሎባቸዋል። ምስል፦ SNNPR

የደቡብ አትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባል ወይዘሮ ታደለች ታሪኩ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶክተር አወቀ ሃምዛዬ ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል ናቸው ፡፡ ዋናው ዓላማቸው ከወከላቸው ሕዝብ ጋር በልማትና በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር እንደነበር የጠቀሱት ወይዘሮ ታደለች እና ዶክተር አወቀ “ ይሁንእንጂ የዞኑ አመራሮች የተለያዩ ሳንካዎችን በመፍጠር ውይይቱ እንዳይካሄድ እያደረጉ ይገኛሉ “ ብለዋል ፡፡

“ በድምጹ ከወከለን ህዝብ ጋር አንዳንገናኝ በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ተከለከልን “ ሲሉ በአማሮ ዞን የሚገኙ  የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት አባላት አመለከቱ ፡፡ ምስል፦ Ethiopian Press Agency

የዞኑ ባለሥልጣናት ምን ይላሉ ?

ዶቼ ቬለ DW የህዝብ ተወካዮቹን ቅሬታ አስመልክቶ ያነጋገራቸው  የዞኑ አመራሮች በበኩላቸው ውይይቱን ሊካሄድ ያልቻለው ተወካዮቹ ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ ለማድረግ ሳይሆን በአካባቢው ካለው የፀጥታ ሁኔታ በመነሳት ነው ብለዋል ፡፡ ተወካዮቹ ከህዝብ እንዳይገኛኙ የሚከለክል ምንም ምክንያት የለም የሚሉት የአማሮ ዞን ምክር ቤት  ምክትል ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ወረደ ወርቁ “ አሁን ላይ የዞኑ የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም ፡፡ ውይይቱን ለማካሄድ ተብሎ ሌላ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ለማድረግ በማሰብ እንጂ ለመከልከል አይደለም “ ብለዋል ፡፡

ከክልከላው ጀርባ

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ አንዱና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዶክተር አወቀ ሃምዛዬ በአካባቢው መለስተኛ የፀጥታ ችግር ቢኖርም የክልከላው ዓላማ ግን ሌላ ነው ይላሉ ፡፡ አማሮ ከፍተኛ የሙስና ችግሮች ያሉበት መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር አወቀ “ የጥቅም መረቦችን በመዘርጋት ፋይናንስ መምሪያ በማያውቀው ሁኔታ ቼኮችን በግለሰቦች እጅ በማስገባት የገንዘብ ምዝበራ እየተካሄደ ነው ፡፡ አሁን በዞኑ የሚስተዋሉትን የመልካም አስተዳደር ፤ የሙስናና የወንጀል ድርጊቶችን ህዝቡ በውይይቱ ያነሳል  በሚል ሆን ብሎ ችግሮች እንዳይጋለጡ  ለማፈን የተደረገ ነው “ ብለዋል ፡፡

የህዝብ ተወካዮቹ ከህዝብ እንዳይገኛኙ የሚከለክል ምንም ምክንያት የለም የሚሉት የአማሮ ዞን ምክር ቤት  ምክትል ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ወረደ ወርቁ “ አሁን ላይ የዞኑ የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም ፡፡ምስል፦ SNNPR

የዞኑ ባለሥልጣናት ውይይቱን እንዳይካሄድ የሚያደርጉት በሙስና ዙሪያ ይፈጸማል የሚባለውን ጥርጣሬ ህዝቡ እንዳያጋልጥ ነው እየተባላችሁ ነው ?  ለዚህ ምን ምላሽ አላችሁ ? ሲል ዶቼ ቬለ የዞኑን ምክትል ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ወረደን ጠይቋል ፡፡  የቅሬታ አቅራቢዎቹን ወቀሳ ያስተባበሉት አቶ ወረደ ግን “ በዞኑ በተባለው ሁኔታ የተገመገመ ነገር የለም “ በሚል በአጭሩ መልሰዋል፡፡ደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ርዕሰ-መስተዳድሮች ተሾመላቸው

የህዝብ ተመራጮቹ በዞኑ አጋጥሞናል ያሉትን ክልከላ ለየተወከሉባቸው ምክር ቤቶች አቤቱታቸውን በማቅረብ ምላሽ እየጠበቁ አንደሚገኙም ተናግረዋል ፡፡ ዶቼ ቬለ የህዝብ ተወካዮችንና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አስተያየትን ለማካትት ያደረገው ጥረት ሃላፊዎቹን ማግኘት ባለመቻሉ ሊሳካ አልቻለም፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW