ዘንድሮ ምርት ሊቀንስ ይችላል
ሐሙስ፣ ሰኔ 3 2013
ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል በዘንደሮ የበልግ ምርት እስከ 35 ሚሊዮን ኩንታል የምርት መቀነስ ሊያጋጥም እንደሚችል የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ሰሞኑን ያካሄደው የቅድመ ትንበያ ጥናት እንደሚያሳየው በክልሉ የበልግ ዝናብ ስርጭት መዛባትና የተምች ተባይ መስፋፋት ለምርት መቀነስ ትንበያው በምክንያት ተቀምጠዋል።ቢሮው በክልሉ የተከሰተውን የተምች ተባይ የመከለላከል ስራዎችንም በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጸዋል። ምክትል የቢሮ ሃላፊውን ያነጋገረው የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ