1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖች አቤቱታ

ማክሰኞ፣ የካቲት 26 2011

በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ተከስተው በነበሩ ግጭቶች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ተገቢውን ድጋፍ ባለማግኘታችው በችግር ላይ መውደቃቸውን እየተናገሩ ነው።

Äthiopien Vertriebene beklagen fehlende Hilfeleistung l Abera Willa
ምስል DW/S. Wegayehu

«የክልሉ የአደጋ ስጋት መከላከል ኮሚሽን ምላሽ ሰጥቷል»

This browser does not support the audio element.

  በአሁኑ ወቅት አልፎ አልፎ በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር የተነሳም ወደ ቀድሞ አካባቢያቸው ለመመለስ ሥጋት እንዳደረባቸው ተፈናቃዮቹ ለዲ ደብሊው ገልጸዋል። የደቡብ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የዕርዳታ አቅርቦቱ አልፎ አልፎ በተለያዩ ምክንያቶች ከሚያጋጥመው የቀናት መዘግየት በስተቀር በተያዘው ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ ይገኛል ብሏል።  ወደ ቀድሞ ቀዬያቸው ለመመለስ ያጋጠማቸውን የፀጥታ ሥጋት ለመቅረፍም ከፌደራሉ የሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር በጥምረት እየተሠራ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ አስታውቋል። ተፈናቃዮቹን እና የኮሚሽኑን የሥራ ኃላፊ ያነጋገረው የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW