ማስታወቂያ
በድሬደዋ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በይፋ ተጀምሯል። አሁን ባለው አቅም በቀን አንድ መቶ ናሙናዎችን መመርመር ይችላል ተብሏል - ላብራቶሪው።
የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በውሰት የሰጠውን የመመርመርያ ማሽን ወደ ስራ ለማስገባት ሲደረግ የነበረው የቅድመ ዝግጅት ተግባር ያጠናቀቀው ምርመራ ማዕከል የምርመራ ስራውን በይፋ ትናንት ጀምሯል።የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና የመስተዳድሩ ምክትል ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ የምርመራ ላቦራቶሪውን በይፋ ስራ አስጀምረዋል።
