በድሬዳዋ ኮሌራ 3 ሰዎች ገደለ
ረቡዕ፣ መስከረም 23 2016የድሬዳዋ የመስተዳድሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ወቅታዊ የጤና ችግሮችን አስመልክቶ ለሚዲያ ተቋማት በሰጡት መግለጫ ቁጥራቸው ከፍ እያለ ከመጡ በሽታዎች ደንጊ ፣ ወባ እና ኮሌራ ዋነኛ መሆናቸውን ገልፀው በመስተዳድሩ በተከሰተው በዚህ ወረርሽኝ ከተያዙ ሰዎች ሶስት መሞታቸውን አስታውቀዋል ።በጎርጎሪዮሳዊው 2023 በኮሌራ የሚያዘው ሰው ቁጥር ጨምሯል
በደንጊ ትኩሳት የተያዙ ሰዎች ቁጥር ባለፉት ሦስት ወራት ከፍ እያለ መምጣቱን የጠቀሱት ኃላፊዋ የዝናብ ወቅትን ተከትሎ በሚራቡ የቢንቢ ትንኞች የሚከሰተቱን የደንጊ እና ወባ በሽታዎች ለመከላከል ቢንቢን ማጥፋት እንደሚገባ ጠቅሰው ህብረተሰቡም የበኩሉን ማድረግ አለበት ብለዋል።የአጣዳፊ ተቅማጥና ተውከት ወረርሽኝ በኢትዮጵያ
አቶ ኢብራሂም አብዱልሀሚድ የተባሉ የጤና ባለሞያ በአስተዳደሩ እየተከሰተ ስላለው ኮሌራ ህክምና እና ሊወሰዱ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ዙርያ ለዶቼቬለ በስልክ በሰጡት አስተያየት ሁሉም ተቋም በሽታውን ለማከም ዝግጁ መሆኑን እና እስካሁን ለተከሰቱትም እያከምን እና እየዳኑ ናቸው ብለዋል። ሰዎች ህመሙ እንደጀመራቸው ህክምና ማግኘት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። አቶ ኢብራሂም በሽታውን ለመከላከል በህብረተሰቡ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎችም አስረድተዋል።
እስካሁን በአስተዳደሩ እየተከሰተ ያለውን የአጣዳፊ ተውከት እና ተቅማጥ በሽታን የመከላከል ስራ ከቁጥጥር ውጭ አለመውጣቱን የገለጠው ጤና ቢሮ ድንገት ከቁጥጥር ውጭ ቢሆን ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች ሳይደናቀፉ ህክምና የሚሰጥበት የተለየ ህክምና መስጫ ማዕከል መቋቋሙን ገልፃል።
ኮሌራ በድሬድዋ
የጤና ቢሮው ከወር በፊት በሰጠው መግለጫ ከድሬደዋ የገጠር ቀበሌዎች አንዱ በሆነው ጀልዴሳ አካባቢ ኮሌራ ተከስቶ እንደነበር ገልፃል ።ለታማሚዎች በተደረገ የህክምና ክትትል እና የአካባቢውን ውሀ በማከም ወረርሽኙን ባለበት መከላከል መቻሉንም አስታውቋል።የኮሌራ በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የተያዘው እቅድቢሮው በወቅቱ መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ አይሁን እንጂ ብዙም ሳይቆይ በሌላ አካባቢ ወረርሽኙ መከሰቱን እና በከተማ በሚገኙ ህክምና ተቋማት ህክምና ሲሰጥ እንደነበር መረጃዎች ሲወጡ ቆይተዋል።ቢሮው አሁን ለሚዲያ በሰጠው መረጃ ሶስት መቶ ሰባ አራት ያህል ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን እና ሶስት ሰዎች በበሽታው መሞታቸውን ገልፃል።የታማሚዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል ያሉት የመስተዳድሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም አሁንም ግን ስጋት መሆኑን ተናግረዋል። ምክንያቱም ወረርሽኙ በሁሉም አካባቢ ባለመጥፋቱ እንደሆን አስረድተዋል። ኅብረተሰቡ ሳይበስሉ የሚመገባቸውን ምግቦች እንዲተው የበሽታው ምልክት የሆኑ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስና ተቅማጥ ምልክቶች ሲያጋጥሙት ወደ ህክምና ተቅዋም በአፋጣኝ እንዲመጣ ጥሪ ቀርቧል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ