በድሬዳዋ የትግራይ ተወላጆች አቤቱታ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 7 2013
ማስታወቂያ
የፌደራል መንግስት “ህግ ማስከበር” በሚል በህወሀት ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ በድሬደዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጀች ስራ እንዲያቆሙ እና እንዲታሰሩ መደረጉን በአንዳንድ ቦታዎችም መሸማቀቅ እየደረሰብን ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፡፡ የድሬደዋ መስተዳድር በበኩሉ ለህዝቡ ስጋት ናቸው በሚል የታሰሩ ሰዎች እየተጣራ መፈታታቸውንና በአሁኑ ሰዓት ሃያ ሶስት ሰዎች ብቻ በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጿል፡፡መሳይ ተክሉ ቅሬታዎቹንና እና መስተዳድሩ የሰጠውን መልስ ያካተተ ዘገባ አጠናቅሯል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ