1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን በከፍተና ተመራማሪነትና የምርምር ሥራዎችን በማስተባበር ከሚሰሩት ኢትዮጲያዊ ሙሁር

ማክሰኞ፣ መስከረም 10 2015

አውሮፓ ውስጥ በተለይም በጀርመንና ስዊድን የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት ዶክተር ወልደሩፋኤል ብርሃነ የሥራ ዓለም ልምዳቸውም ከተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ከመጡ ተመራማሪዎች ጋር በከፍተኛ ተመራማሪነትና በተለይ በአውሮፓ ሕብረት በሚደገፉ ምርምሮች በአስተባባሪነት ሠርተዋል።

Äthiopien | Äthiopischer leitender Forscher Dr. Welderufeal Brhane
ምስል privat

ኢትዮጵያዊው ሙሁርና ተመራማሪ ዶክተር ወልደሩፋኤል ብርሃነ

This browser does not support the audio element.

በአውሮፓ በተለይም በስዊድንና በጀርመን በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በሞባይል ስልክ ሥርዓትና መተግበሪያ፣ በቴሌኮሚዩኒኬሽን መሰረተልማት እንዲሁም ገመናን ከደህንነት፣ ግለ ጠባይና ሕግ አንጻር በተመለከተ በመመራመር የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩና አሁን በከፍተኛ ተመራማሪነትና የምርምር ፕሮጀክቶችን በማስተባበር ላይ ይገኛሉ ዶክተር ወልደሩፋኤል ብርሃነን። 
የዛሬ 10 ዓመት ግድም ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ለትምህርት የመጡት ዶክተር ወልደሩፋኤል እዚህ በአውሮፓ ቆይታቸው በሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ደረጃ በስዊድንና ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ውስጥ በሚገኙ የኒቨርስቲዎች እንደተማሩ አጫውተውናል። 
የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ስዊድን አገር የተማሩት ዶክተር ወልደሩፋኡል በቆይታቸው በሞባይል መተግበሪያዎችና ሥርአት እንዲሁም በቴሌኮሚዩኒኬሽን መሰረተ ልማት ዝርጋታ በተመለከተ  ምርምር በማካሄድ እውቀት መሸመታቸውን አጫውተውናል።
እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 ለሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ወደ ጀርመን የመጡት ዶክተር ወልደሩፋኤል ለዶክትሬት ትምህርታቸው የመረጡት የምርምር ዘርፍ ለየት ያለና ተመራማሪዎች ብዙ ትኩረት ያልሰጡት እንደሆነ የቅርብ ረዳቶቻቸው ይናገራሉ። ዶክተር ወልደሩፋኤል የሰዎች ገመና ከሕግና የሰዎች ጸባይ እንዲሁም አርተፊሻል ኢንተለጀንስን ከመሳሰሉ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ጋር በማጣመር ምርምራቸውን እዚህ ጀርመን አገር  ሰርቷል። 
አውሮፓ ውስጥ በተለይም በጀርመንና ስዊድን የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት ዶክተር ወልደሩፋኤል ብርሃነ የሥራ ዓለም ልምዳቸውም ከተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ከመጡ ተመራማሪዎች ጋር በከፍተኛ ተመራማሪነትና በተለይ በአውሮፓ ሕብረት በሚደገፉ ምርምሮች በአስተባባሪነትም ሠርተዋል።  
የተለየ ባሕል፣ ወግና አስተዳደግ ይዞ ወደ አውሮፓ  የመጣ ሰው  እዚህ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እራሱን አላምዶ ለመሄድ ብዙ ጊዜ ሲቸገር ይስተዋላል። እንደ ኢትዮጵያ ካለ ማኅበራዊ መስተጋብሩ ከጠነከረ ሐገር ለመጣ ሰው አውሮፓ ውስጥ ተላምዶ ለመኖር መቸገር ብዙም እንግዳ አይደለም። በተለይም ቋንቋ። እንደዚህ አይነት ፈታኝ ሁኔታዎች እንዴት አለፉት ብለን ጠየቅናቸው ዶክተር ወልደሩፋኤልን። እሳችው እንዳሉን በተለይ የባሕል አለመመሳሰል ከፍተኛ ተግዳሮት ሆኖባቸው ነበር።
ዶክተር ወልደሩፋኤል በከፍተኛ ተመራማሪነትና የምርምር ሥራዎችን በማስተባበር ካካበቱት ልምድ አኳያም ይሁን በአጠቃላይ ጀርመን ውስጥ ከተመለከቱት ፤ እንደው ይኽስ በሐገሬ በሆነ ብለው የሚመኙት ነገር አለ ይኾን? ጠየቅናቸው። ከቴክኖሎጂው በላይ ጀርመን አገር ያለው ሰው በሰውነቱ ብቻ የመከበርና ሰላም እጅጉ እንደሚያስቀናቸውና ይህ በአገራቸው ቢሆን እንደሚመኙት አጫውተውናል።
በጀረመን ሐገር በከፍተኛ ተመራማሪነትና የምርምር ሥራዎችን በማስተባበር ሥራ ላይ ከሚገኙት ኢትዮጵያዊው ምሁርና ተመራራማሪ ዶክተር ወልደሩፋኤል ብርሃነ ጋር የነበረን ቆይታ በዚሁ ተጠናቋል።

ምስል Brenda Asirvadappan/DW

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር 

ሽዋዬ ገገሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW