1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን የፀረ አይሁድ እንቅስቃሴ እና የመንግስት የጸና አቋም

ዓርብ፣ ጥቅምት 9 2016

በርሊን ውስጥ በአይሁዳውያን ምኩራብ ላይ የፀረ አይሁዳውያን ጥቃት ከደረሰ በኋላ የጀርመን መንግስት በፀረ አይሁዳውያን እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል። መዲናዪቱ በርሊን ውስጥ ምንም እንኳ የከፋ ጉዳት ባያደርስም የፀረ ሴማዊነት እንቅስቃሴ አራማጆች ጥቃት ሰንዝረዋል።

የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ
የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ምስል Annegret Hilse/REUTERS

ፀረ-ሴማዊነት በጀርመን ተቀባይነት የለዉም፤ የጀርመን መንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገ ነዉ

This browser does not support the audio element.

ያዝነዉ ሳምንት ሃሙስ በርሊን ውስጥ በአይሁዳውያን ምኩራብ ላይ የፀረ አይሁዳውያን ጥቃት ከደረሰ በኋላ የጀርመን መንግስት በፀረ አይሁዳውያን እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል። መዲናዪቱ በርሊን ውስጥ ምንም እንኳ የከፋ ጉዳት ባያደርስም የጸረ ሴማዊነት እንቅስቃሴ አራማጆች ተቀጣጣይ ነገር መወርወሩን ተከትሎ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስን ጨምሮ ፖለቲከኞች መረር ያለ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል። በጀርመን መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀውን ሃማስን መደገፍም ሆነ እስራኤልን መቃወም በህግ ጭምር በታገደባት ጀርመን ባለፉት ቀናት ፍልስጥኤማውያኑን የሚደግፉ እና እስራኤልን የሚያወግዙ ሰልፎች መታየታቸውን ተከትሎ በሰልፉ የሚሳተፉትንም ሆነ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል። በእስራኤል ሃማስ ጦርነት ጀርመን የምትከተለው ፖሊሲባለፈው ረቡዕ በበርሊን የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ እና ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል የተባሉ ከ170 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቧል። ጀርመን ከዚህ በኋላ የዜግነት ጥያቄ ለሚያቀርቡ በእስራኤል ህልውና የሚምኑ መሆን እንዳለባቸውም ከወዲሁ እየገለጸች ነው። 

በርሊን ውስጥ ትናንት በአይሁዳውያን ምኩራብ ላይ የጸረ አይሁዳውያን ጥቃት ከደረሰ በኋላ የጀርመን መንግስት በጸ አይሁዳውያን እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ  ሊወስድ ነው። መዲናዪቱ በርሊን ውስጥ ምንም እንኳ የከፋ ጉዳት ባያደርስም በጸረ ሴሜቲክ እንቅስቃሴ አራማጆች  ተቀጣጣይ ነገር መወርወሩን ተከትሎ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስን ጨምሮ ፖለቲከኞች መረር ያለ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።ምስል Michael Kappeler/dpa/picture alliance


ይልማ ኃይለ ሚካኤል 


ታምራት ዲንሳ 
አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW