በጃፓን ያልተሳካው የኢትዮጵያ አትሌቶች ተልዕኮ
ቅዳሜ፣ መስከረም 10 2018
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ስትካፈልበት ከሰነበተችው 20ኛው የቶኪዮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ሳታገኝ የመጨረሻውን ቀን እየጠበቀች ነው። ዛሬ ኢትዮጵያዉያ ሜዳሊያ ልታገኝ ትችላለች ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የሴቶች የ5000 ሜትር ውድድር ያለ ሜዳሊያ ተጠናቋል።
በውድድሩ ሜዳሊያ የማግኘት ቅድመ ግምት አግኝታ የነበረው ጉዳፍ ጸጋይ አምስተኛ በመሆን አጠናቃለች። ኬንያዉያኑ ብአትሪክ ቺቤት እና ፌዝ ኪፒገን የወርቅ እና የብር ሜዳሊያውን ለኬንያ አስገኝተዋል።
በቶኪዮ የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ለሜዳሊያ ብቸኛ ተስፋ የሰነቀችበት ነገ እሁድ የሚካሄደው የወንዶች የአምስት ሺ ሜትር ውድድር ብቻ ነው ፤ እሱም ቢሆን በጠባብ ዕድል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ በሃያኛው የዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለምን ዉጤት አጣች ? የመስኩ ባለሞያዎችስ በዚህ ላይ ምን ይላሉ ?
ኃይማኖት ጥሩነህ