1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጅቡቲ በአፋሮች እና በሶማሌዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ ሶስት ሰዎች ተገደሉ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 27 2013

በጅቡቲ በአፋሮች እና በሶማሌዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ ዐቃቤ ሕግ አስታውቀዋል ። ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከትናንት በስቲያ እሁድ በዋና ከተማዋ ጅቡቲ የተለያዩ ክፍሎች ኢትዮጵያ እና ኤርትራን በሚያዋስነው የአገሪቱ ክፍል በሚገኙት አፋሮች እና በሶማሌ የኢሳ ጎሳ አባላት መካከል ነው።

Menschenrechtsorganisation AFAR | Geas Ahmed, Chairman
ምስል Geas Ahmed

በጂቡቲ የአፋር እና ኤሳ ግጭት ሰዎች ተገደሉ

This browser does not support the audio element.

 በጅቡቲ በአፋሮች እና በሶማሌዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ ዐቃቤ ሕግ አስታውቀዋል ። ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከትናንት በስቲያ እሁድ በዋና ከተማዋ ጅቡቲ የተለያዩ ክፍሎች ኢትዮጵያ እና ኤርትራን በሚያዋስነው የአገሪቱ ክፍል በሚገኙት አፋሮች እና በሶማሌ የኢሳ ጎሳ አባላት መካከል ነው። የአፋር የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ገአስ አህመድ በተለይ ከዶይቼ ቬሌ ጋር በነበራቸው አጭር ቃለ ምልስ በግጭቱ የተገደሉ ሰዎች 6 መድረሳቸውን ተናግረዋል። አቶ ገአስን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት አነጋግሬአቸው ነበር።

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW