1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጉራጌ ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

ሰኞ፣ ግንቦት 10 2012

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በማረቆ እና በመስቃን መካከል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና አንድ የጉራጌ ዞን ባለሥልጣን ተናገሩ። ግጭቱ የተቀሰቀሰው የቀድሞው መስቃን እና ማረቆ ወረዳ ለሁለት ሲከፈል የዘጠኝ ቀበሌዎች ይገባኛል በፈጠረው ውዝግብ ነው ተብሏል።

Karte Äthiopien Ethnien EN

በጉራጌ ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በማረቆ እና በመስቃን መካከል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና አንድ የጉራጌ ዞን ባለሥልጣን ተናገሩ። ግጭቱ የተቀሰቀሰው የቀድሞው መስቃን እና ማረቆ ወረዳ ለሁለት ሲከፈል የዘጠኝ ቀበሌዎች ይገባኛል በፈጠረው ውዝግብ ነው ተብሏል።

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በማረቆ እና በመስቃን መካከል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና አንድ የጉራጌ ዞን ባለሥልጣን ተናገሩ። ግጭቱ የተቀሰቀሰው የቀድሞው መስቃን እና ማረቆ ወረዳ ለሁለት ሲከፈል የዘጠኝ ቀበሌዎች ይገባኛል በፈጠረው ውዝግብ መሆኑን የሀዋሳው የዶይቼ ቬለ ወኪል ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዘግቧል። 
የአሁኑ ግጭት የተቀሰቀሰው በዞኑ የማረቆ እና የመስቃን ቤተ ጉራጌ ማህበረሰብ አባላት ተቀላቅለው በሚኖሩበት ምስራቅ መስቃን ወረዳ ባቴ ሌጃኖ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው። 
አንድ የአካባቢው ነዋሪ ግጭቱ በወሰን ይገባኛል ጥያቄ መቀስቀሱን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል። ግለሰቡ እንዳሉት እስከአሁን ከሁለቱም የማህበረሰብ አባላት አስር ሰዎች ሲሞቱ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ የመኖሪያ ቤቶችና ንብረቶች ወድመዋል።  ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፈለቀ አባተ ግጭቱ መቀስቀሱን አረጋግጠዋል። የግጭቱ መነሾ በግለሰቦች መካከል እንጂ በሁለት ማኅበረሰቦች አይደለም ያሉት አቶ ፈለቀ የሟቾች ቁጥር ስድስት ብቻ ነው ብለዋል። 
በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በማረቆና በመስቃን ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች ከሁለት ዓመታት በፊት ተመሳሳይ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር። በወቅቱ እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሲሞቱ በርካቶች ከቀያቸው ተፈናቅለው ነበር። 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

እሸቴ በቀለ
 
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW