በጉራፈርዳ ወረዳ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ
ሰኞ፣ ግንቦት 30 2013![Karte Äthiopien englisch](https://static.dw.com/image/6473754_800.webp)
ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ታጣቂዎች ከአራት ሺህ በላይ ነዋሪዎችን አፈናቀሉ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት መፈናቀሉ የተከሰተው የታጠቁ ቡድኖች ዓርብ ዕለት ስድስት የፀጥታ አባላትን ገድለው ወደ መንደሮቹ ከገቡ በኋላ ነው። ታጣቂዎቹ ቅዳሜና እሁድ በወረዳው ጋቢጣና ሰመርታ በተባሉ ቀበሌያት የመኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል፣ በማሳ ላይ የነበረ ሰብልም አውድመዋል። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ የፀጥታ ባለሥልጣናት በቁጥር ባይጠቅሱም በወረዳው በፀጥታ አባላት ላይ ጥቃት መድረሱንና የመኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን አረጋግጠዋል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ